እንደዚህ አድርጎ እግዚአብሔር በረባዳው ስፍራ የነበሩትን ከተሞች ሲያጠፋ አብርሃምን ዐሰበው፤ ስለዚህም የሎጥ መኖሪያ የነበሩትን ከተሞች ካጠፋው መዓት ሎጥን አወጣው።
ምሳሌ 21:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጻድቁ የክፉዎችን ቤት ልብ ብሎ ይመለከታል፤ ክፉዎችንም ያጠፋቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጻድቅ ስለ ኀጥእ ቤት ያስባል፥ ኀጥኣንም ለጥፋት እንደ ተገለበጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጻድቁ አምላክ በክፉዎች ቤት የሚደረገውን ሁሉ ይመለከታል። ክፉዎችንም አሸቀንጥሮ በመጣል ያጠፋቸዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የክፉዎች ልብ ጽድቅን አያውቅም፥ ክፋትም ኃጥአንን ያከፋቸዋል። |
እንደዚህ አድርጎ እግዚአብሔር በረባዳው ስፍራ የነበሩትን ከተሞች ሲያጠፋ አብርሃምን ዐሰበው፤ ስለዚህም የሎጥ መኖሪያ የነበሩትን ከተሞች ካጠፋው መዓት ሎጥን አወጣው።
ጥበበኛ የሆነ እነዚህን ነገሮች ያስተውላል፤ አስተዋይም እነዚህን ነገሮች ይረዳል። የእግዚአብሔር መንገድ ቅን ነውና፤ ጻድቃን ይሄዱበታል፤ ዐመፀኞች ግን ይሰናከሉበታል።
“ሰዶምንና ገሞራን እንደ ገለበጥኋቸው፣ አንዳንዶቻችሁን ገለበጥሁ፤ ከእሳት እንደ ተነጠቀ ትንታግ ሆናችሁ፤ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፤” ይላል እግዚአብሔር።