በተለይም ‘አገልጋይህ ያዕቆብ ከኋላችን እየመጣ ነው’ ማለትን አትዘንጉ።” ይህንም ያዘዘው፣ “ዔሳው ከእኔ ጋራ ከመገናኘቱ በፊት እጅ መንሻዬ አስቀድሞ ቢደርሰው ምናልባት ልቡ ይራራና በሰላም ይቀበለኛል” ብሎ ስላሰበ ነበር።
ምሳሌ 19:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ብዙ ሰዎች በገዥ ዘንድ ሞገስ ለማግኘት ያሸረግዳሉ፤ ስጦታን ከሚሰጥ ሰው ጋራ ሁሉም ወዳጅ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ብዙ ሰዎች ለጋሱን ያቈላምጣሉ፥ ስጦታ ለሚሰጥም ሁሉ ወዳጅ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ብዙ ሰዎች የለጋሥ ሰውን ወዳጅነት ይፈልጋሉ፤ ስጦታን ለሚሰጥ ሰው ሁሉም ወዳጁ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብዙ ሰዎች በነገሥታት ፊት ያገለግላሉ፥ ነገር ግን የሰው ጽድቁና ሀብቱ ከእግዚአብሔር ዘንድ ናቸው፤ ክፉ ሁሉም የሰው መዘባበቻ ይሆናል። |
በተለይም ‘አገልጋይህ ያዕቆብ ከኋላችን እየመጣ ነው’ ማለትን አትዘንጉ።” ይህንም ያዘዘው፣ “ዔሳው ከእኔ ጋራ ከመገናኘቱ በፊት እጅ መንሻዬ አስቀድሞ ቢደርሰው ምናልባት ልቡ ይራራና በሰላም ይቀበለኛል” ብሎ ስላሰበ ነበር።
በዚህ ጊዜ ዮሴፍ የምድሪቱ ገዥ ነበር፤ ለአገሩ ሰዎች ሁሉ እህል የሚሸጥላቸው እርሱ ነበር። የዮሴፍ ወንድሞችም እንደ ደረሱ፣ ከፊቱ ቀርበው ወደ ምድር ለጥ ብለው እጅ ነሡት።
ወደ ቤትም በገቡ ጊዜ ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋራ አዩ፤ ተንበርክከውም ሰገዱለት። ሣጥኖቻቸውን ከፍተው ወርቅ፣ ዕጣን፣ ከርቤም አቀረቡለት።