ምሳሌ 19:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ትእዛዞችን የሚያከብር ሕይወቱን ይጠብቃል፤ መንገዱን የሚንቅ ግን ይሞታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ትእዛዝን የሚጠብቅ ነፍሱን ይጠብቃል፥ መንገዱን ቸል የሚል ግን ይጠፋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ትእዛዝን የሚጠብቅ በሕይወት ይኖራል፤ የእግዚአብሔርን ቃል የሚንቅ ግን ይጠፋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ትእዛዛትን የሚጠብቅ ነፍሱን ይጠብቃል፤ መንገዶቹን የሚያቃልል ግን ይጠፋል። |
እነሆ፤ ሁሉ ነገር ከተሰማ ዘንድ፣ የነገሩ ሁሉ ድምዳሜ ይህ ነው፤ አምላክን ፍራ፤ ትእዛዞቹንም ጠብቅ፤ ይህ የሰው ሁለንተናዊ ተግባሩ ነውና።
ነገር ግን ድምፄን ስሙ፤ እኔም አምላክ እሆናችኋለሁ፤ እናንተም ሕዝቤ ትሆናላችሁ፤ መልካም እንዲሆንላችሁም፣ ባዘዝኋችሁ መንገድ ሁሉ ሂዱ ብዬ አዘዝኋቸው።