ምሳሌ 18:22 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሚስት የሚያገኝ መልካም ነገርን ያገኛል፤ ከእግዚአብሔርም ዘንድ ሞገስን ይቀበላል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሚስት ያገኘ በረከትን አገኘ፥ ከጌታም ሞገስን ይቀበላል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሚስት ከእግዚአብሔር የምትሰጥ በረከት ስለ ሆነች ሚስት ካገኘህ መልካም ነገር አግኝተሃል ማለት ነው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደግ ሚስትን ያገኘ ሞገስን አገኘ፥ ከእግዚአብሔርም ደስታን ተቀበለ። ደግ ሴትን የፈታ ደስታን አጣ፥ አመንዝራዪቱንም የሚያኖር አላዋቂና ኀጢአተኛ ነው። |
አምላክ ከፀሓይ በታች በሰጠህ በዚህ ትርጕም የለሽ የሕይወት ዘመን ሁሉ፣ ከንቱ በሆኑትም ቀኖችህ ሁሉ ከምትወድዳት ሚስትህ ጋራ ደስ ይበልህ፤ በሕይወትህና ከፀሓይ በታች በምትደክምበት ነገር ሁሉ ይህ ዕድል ፈንታህ ነውና።
እንዲሁም የሟቹ ስም ከወንድሞቹ መካከልና ከአገሩ ደጅ እንዳይጠፋ፣ የሟቹን ስም በርስቱ ላይ ለማስጠራት የመሐሎን ሚስት የነበረችው ሞዓባዊት ሩትን አግብቼአታለሁ፤ እናንተም ዛሬ ምስክሮች ናችሁ።”