ወንድሞቻቸው የአሮን ዘሮች እንዳደረጉት ሁሉ፣ እነዚህም በንጉሥ ዳዊት፣ በሳዶቅ፣ በአቢሜሌክ እንዲሁም የካህናቱና የሌዋውያኑ ቤተ ሰብ አለቆች ባሉበት ዕጣ ተጣጣሉ፤ የበኵሩም ቤተ ሰቦች እንደ ትንሹ ወንድም ቤተ ሰብ እኩል ዕጣ ተጣለላቸው።
ምሳሌ 18:18 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዕጣ መጣጣል ሙግትን ያስቆማል፤ ኀይለኛ ባላንጣዎችንም ይገላግላል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዕጣ ክርክርን ትከለክላለች፥ በኃያላንም መካከል ትበይናለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዕጣ መጣል ጠብን ያበርዳል፤ ሁለት ጠንካራ ተከራካሪዎችንም ይገላግላል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዕጣ ክርክርን ያስተዋል፥ በኀያላንም መካከል ይለያል። |
ወንድሞቻቸው የአሮን ዘሮች እንዳደረጉት ሁሉ፣ እነዚህም በንጉሥ ዳዊት፣ በሳዶቅ፣ በአቢሜሌክ እንዲሁም የካህናቱና የሌዋውያኑ ቤተ ሰብ አለቆች ባሉበት ዕጣ ተጣጣሉ፤ የበኵሩም ቤተ ሰቦች እንደ ትንሹ ወንድም ቤተ ሰብ እኩል ዕጣ ተጣለላቸው።
በዚህ ጊዜ የሕዝቡ መሪዎች መኖሪያቸውን በኢየሩሳሌም አደረጉ፤ ከቀረው ሕዝብ ከዐሥር አንዱ እጅ በቅድስቲቱ ከተማ በኢየሩሳሌም፣ የቀሩት ዘጠኙ እጅ ደግሞ በየራሳቸው ከተሞች እንዲኖሩ ዕጣ ተጣጣሉ።
ከዚያ በኋላ ሳኦል፣ “ትክክለኛውን መልስ ስጠኝ” ሲል ወደ እስራኤል አምላክ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ ዕጣው በሳኦልና በዮናታን ላይ ወደቀ፤ ሕዝቡም ነጻ ሆነ።