ምሳሌ 16:23 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጠቢብ ሰው ልብ አንደበቱን ይመራል፤ ከንፈሮቹም ዕውቀትን ያዳብራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጠቢብ ልብ አፉን ያስተምራል፥ ለከንፈሩም ትምህርትን ይጨምራል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የጥበበኛ ሰው አእምሮ ንግግሩን ይቈጣጠራል፤ ከአፉም የሚወጣው ንግግር ትምህርትን ያስፋፋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጠቢብ ልብ ከአፉ ይታወቃል፥ በከንፈሩም ዕውቀትን ይለብሳል። |
የክርስቶስ ቃል በሙላት ይኑርባችሁ፤ እርስ በርሳችሁ በጥበብ ሁሉ ተማማሩ፤ ተመካከሩ፤ በመዝሙርና በማሕሌት፣ በመንፈሳዊም ቅኔ በማመስገን በልባችሁ ለእግዚአብሔር ዘምሩ።