ምሳሌ 16:11 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሐቀኛ መስፈሪያና ሚዛን ከእግዚአብሔር ናቸው፤ በከረጢት ውስጥ ያሉት መመዘኛዎችም ሁሉ ሥራዎቹ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እውነተኛ ሚዛንና መመዘኛ የጌታ ናቸው፥ የከረጢት መመዘኛዎች ሁሉ የእርሱ ሥራ ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሚዛንና መስፈሪያ ትክክል እንዲሆኑ፥ ለሽያጭ የሚቀርቡት ዕቃዎች ሁሉ ሚዛናቸው የተስተካከለ እንዲሆን የእግዚአብሔር ትእዛዝ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔር ፍርድ እንደ ሚዛን ውልብልቢት ነው፤ ሥራውም የከረጢት ደንጊያ ነው። |
እንዲህም ትላላችሁ፤ “መስፈሪያውን በማሳነስ፣ ዋጋውን ከፍ በማድረግ፣ በሐሰተኛ ሚዛን በማጭበርበር፣ እህል እንድንሸጥ፣ የወር መባቻ መቼ ያበቃል? ስንዴም ለገበያ እንድናቀርብ፣ ሰንበት መቼ ያልፋል?”