“አሁን ግን እግዚአብሔር አምላካችን ቅሬታ ይተውልን ዘንድ፣ በመቅደሱም ውስጥ ጽኑ ስፍራ ይሰጠን ዘንድ፣ ለጥቂት ጊዜ ቸርነቱን አሳይቶናል፤ ስለዚህ አምላካችን ለዐይናችን ብርሃን ሰጠን፤ በባርነትም ሳለን ለጥቂት ጊዜ ዕረፍት ሰጠን።
ምሳሌ 15:30 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ብሩህ ገጽታ ልብን ደስ ያሰኛል፤ መልካም ዜናም ዐጥንትን ያለመልማል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዐይን ብርሃን ልብን ደስ ያሰኛል፥ መልካም ወሬም አጥንትን ያለመልማል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በፈገግታ የተሞላ ፊት ልብን ያስደስታል፤ የምሥራች ቃልም አጥንትን ያለመልማል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መልካምን ነገር የሚያይ ዐይን ልብን ደስ ያሰኛል፥ መልካም ዜናም አጥንትን ያለመልማል። |
“አሁን ግን እግዚአብሔር አምላካችን ቅሬታ ይተውልን ዘንድ፣ በመቅደሱም ውስጥ ጽኑ ስፍራ ይሰጠን ዘንድ፣ ለጥቂት ጊዜ ቸርነቱን አሳይቶናል፤ ስለዚህ አምላካችን ለዐይናችን ብርሃን ሰጠን፤ በባርነትም ሳለን ለጥቂት ጊዜ ዕረፍት ሰጠን።
እግዚአብሔር ሁልጊዜ ይመራሃል፤ ፀሓይ ባቃጠለው ምድር ፍላጎትህን ያሟላል፤ ዐጥንትህን ያበረታል፤ በውሃ እንደ ረካ የአትክልት ቦታ፣ እንደማይቋርጥም ምንጭ ትሆናለህ።
ከእንግዲህ ወዲህ ሌሊት አይኖርም፤ ጌታ አምላክ ስለሚያበራላቸው የመብራት ወይም የፀሓይ ብርሃን አያስፈልጋቸውም፤ ከዘላለም እስከ ዘላለምም ይነግሣሉ።