መልካም ብታደርግ ተቀባይነትን አታገኝምን? መልካም ባታደርግ ግን፣ ኀጢአት በደጅህ እያደባች ናት፤ ልታሸንፍህ ትፈልጋለች፤ አንተ ግን ተቈጣጠራት።”
ምሳሌ 13:21 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም መጥፎ ዕድል ኀጢአተኛን ይከታተላል፤ ብልጽግና ግን የጻድቃን ዋጋ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ክፉ ነገር ኃጢአተኞችን ያሳድዳቸዋል፥ ጻድቃን ግን መልካሙን ዋጋ ይቀበላሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኃጢአተኞችን በሄዱበት ስፍራ ሁሉ መከራ ይከተላቸዋል፤ ደጋግ ሰዎች ግን የመልካም ሥራቸውን ዋጋ ያገኛሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በደለኞችን ክፉ ነገር ይከተላቸዋል፤ ጻድቃንን ግን መልካም ነገር ያገኛቸዋል። |
መልካም ብታደርግ ተቀባይነትን አታገኝምን? መልካም ባታደርግ ግን፣ ኀጢአት በደጅህ እያደባች ናት፤ ልታሸንፍህ ትፈልጋለች፤ አንተ ግን ተቈጣጠራት።”
ጥፋት ይመጣብሻል፤ ነገር ግን በአስማትሽ እንዴት እንደምታርቂው አታውቂም፤ ወጆ ከፍለሽ ለማስወገድ የማትችዪው፣ ጕዳት ይወድቅብሻል፤ ያላሰብሽው አደጋ፣ ድንገት ይደርስብሻል።
የደሴቲቱ ነዋሪዎች እባብ በእጁ ላይ ተንጠልጥላ ባዩ ጊዜ፣ “ይህ ሰው በርግጥ ነፍስ ገዳይ ነው፤ ከባሕር ቢያመልጥ እንኳ የፍርድ አምላክ በሕይወት እንዲኖር አልፈቀደለትም” ተባባሉ።