ከአባቱ ሞት በኋላ የአክዓብ ቤት ሰዎች አማካሪዎቹ በመሆን ወደ ጥፋት ስለ መሩት፣ የአክዓብ ቤት እንዳደረገው ሁሉ እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገር አደረገ።
ምሳሌ 12:20 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክፋትን በሚያውጠነጥኑ ሰዎች ልብ አታላይነት አለ፤ ሰላምን የሚያራምዱ ግን ደስታ አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ክፉን በሚያስቡ ልብ ውስጥ ተንኰል አለ፥ በሰላም ለሚመክሩ ግን ደስታ አላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ክፋትን በሚያቅዱ ሰዎች ልብ ተንኰል አለ፤ ሰላም የሚገኝበትን ነገር የሚመክሩ ግን ደስታን ያገኛሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ክፉን በሚያስብ ልብ ውስጥ ማታለል አለ፤ ሰላምን የሚወዱ ግን ደስ ይላቸዋል፥ |
ከአባቱ ሞት በኋላ የአክዓብ ቤት ሰዎች አማካሪዎቹ በመሆን ወደ ጥፋት ስለ መሩት፣ የአክዓብ ቤት እንዳደረገው ሁሉ እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገር አደረገ።
ልባቸው ወደ ክፋት ያዘነበለው ሁለቱ ነገሥታት፣ በአንድ ገበታ ዐብረው ይቀመጣሉ፤ እርስ በርሳቸውም ሐሰትን ይነጋገራሉ፤ ነገር ግን የተወሰነው ጊዜ ገና ስለ ሆነ አይከናወንላቸውም።
የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ የሚሠራው እርሱ ነው፤ ክብርን ይጐናጸፋል፤ በዙፋኑ ተቀምጦ ይገዛል፤ በዙፋኑም ላይ ካህን ይሆናል፤ በሁለቱም መካከል የሰላም ምክር ይኖራል።’
በሁሉም ዐይነት ዐመፃ፣ ክፋት፣ ስግብግብነትና ምግባረ ብልሹነት ተሞልተዋል፤ ቅናትን፣ ነፍስ ገዳይነትን፣ ጥልን፣ አታላይነትንና ተንኰልን የተሞሉ ናቸው፤ ሐሜተኞች፣