ምሳሌ 11:30 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጻድቅ ፍሬ የሕይወት ዛፍ ናት፤ ነፍሳትን የሚማርክም ጠቢብ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጻድቅ ፍሬ የሕይወት ዛፍ ናት፥ ነፍሶችንም የሚማርክ እርሱ ጠቢብ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የጻድቅ ሰው ሥራ የዘለዓለም ሕይወትን ያስገኛል፤ ዐመፅ ግን ለሕይወት መጥፋት ምክንያት ይሆናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከጻድቅ ፍሬ የሕይወት ዛፍ ይወጣል። የዐመፀኞች ነፍሳት ግን በድንገት ይወገዳሉ። |
ዐጫጁ አሁንም ቢሆን እንኳ ደመወዙን እየተቀበለ ነው፤ ለዘላለም ሕይወት ይሆን ዘንድ አዝመራውን ይሰበስባል፤ ይህም ዘሪውና ዐጫጁ በጋራ ደስ እንዲላቸው ነው።
መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚናገረውን፣ ጆሮ ያለው ይስማ፤ ድል ለሚነሣ በእግዚአብሔር ገነት ካለው ከሕይወት ዛፍ እንዲበላ አደርገዋለሁ።