አምላኬ ሆይ፤ ልብን እንደምትመረምርና ቅንነትን እንደምትወድድ ዐውቃለሁ፤ እኔም ይህን ሁሉ የሰጠሁት በበጎ ፈቃድና በቀና መንፈስ ነው። አሁንም በዚህ ያለው ሕዝብህ በበጎ ፈቃዱ እንዴት እንደ ሰጠ አይቻለሁ።
ምሳሌ 11:20 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ልበ ጠማሞችን ይጸየፋል፤ በመንገዳቸው ነቀፋ በሌለባቸው ሰዎች ግን ደስ ይሰኛል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልበ ጠማሞች በጌታ ዘንድ አስጸያፊዎች ናቸው፥ በመንገዳቸው ፍጹማን የሆኑ ግን የተወደዱ ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ልበ ጠማሞችን ይጸየፋል። ነቀፋ በሌለበት መንገድ በሚሄዱ ሰዎች ይደሰታል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጠማማ መንገድ በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ ነው፤ በመንገዳቸው ፍጹማን የሆኑ ግን በፊቱ የተመረጡ ናቸው። |
አምላኬ ሆይ፤ ልብን እንደምትመረምርና ቅንነትን እንደምትወድድ ዐውቃለሁ፤ እኔም ይህን ሁሉ የሰጠሁት በበጎ ፈቃድና በቀና መንፈስ ነው። አሁንም በዚህ ያለው ሕዝብህ በበጎ ፈቃዱ እንዴት እንደ ሰጠ አይቻለሁ።