ምሳሌ 10:29 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔር መንገድ ለጻድቃን መጠጊያ፣ ክፉ ለሚያደርጉ ግን መጥፊያቸው ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጌታ መንገድ ያለ ነውር ለሚሄድ አምባ ነው፥ ክፋትን ለሚያደርጉ ግን ጥፋት ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእግዚአብሔር መንገድ ለጻድቃን ከለላ ነው፤ ለክፉ አድራጊዎች ግን መጥፊያቸው ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርን መፍራት ለደግ ሰው ብርታት ነው፥ ጥፋት ግን ክፋት ለሚያደርጉ ነው። |
ጥበበኛ የሆነ እነዚህን ነገሮች ያስተውላል፤ አስተዋይም እነዚህን ነገሮች ይረዳል። የእግዚአብሔር መንገድ ቅን ነውና፤ ጻድቃን ይሄዱበታል፤ ዐመፀኞች ግን ይሰናከሉበታል።