ምሳሌ 10:27 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርን መፍራት ዕድሜን ያረዝማል፤ የክፉዎች ዕድሜ ግን በዐጭር ይቀጫል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታን መፍራት ዘመንን ታረዝማለች፥ የከፉዎች ዕድሜ ግን ታጥራለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርን መፍራት ዕድሜን ያረዝማል፤ ክፉዎች ግን ያለ ዕድሜያቸው በሞት ይቀጫሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርን መፍራት ዘመንን ያረዝማል፤ የኃጥኣን ዕድሜ ግን ያጥራል። |
አንተ ግን፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ ክፉዎችን ወደ ጥፋት ጕድጓድ ታወርዳቸዋለህ፤ ደም የተጠሙ ሰዎችና አታላዮች፣ የዘመናቸውን እኩሌታ አይኖሩም። እኔ ግን በአንተ እታመናለሁ።
ሀብትን በግፍ የሚያከማች ሰው፣ ያልፈለፈለችውን ጫጩት እንደምትታቀፍ ቆቅ ነው፤ በዕድሜው አጋማሽ ትቶት ይሄዳል፤ በመጨረሻም ሞኝነቱ ይረጋገጣል።
“እግዚአብሔር ግን፣ ‘አንተ ሞኝ፤ ነፍስህን በዚህች ሌሊት ከአንተ ሊወስዱ ይፈልጓታል፤ እንግዲህ፣ ለራስህ ያከማቸኸው ለማን ይሆናል?’ አለው።