ምሳሌ 10:24 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክፉ ሰው የፈራው ይደርስበታል፤ ጻድቅ የሚመኘው ይፈጸምለታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የክፉ ሰው ፍርሃት በላዩ ይመጣበታል፥ ለጻድቃንም ምኞታቸው ትሰጣቸዋለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደጋግ ሰዎች የሚፈልጉትን ያገኛሉ፤ ክፉዎች ግን እጅግ የፈሩት ነገር ይደርስባቸዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኃጥእ ወደ ጥፋት ይመለሳል፥ የጻድቅ ምኞቱ ግን በእግዚአብሔር ዘንድ የተወደደች ናት። |
ስለዚህ ችግር እንዲደርስባቸው አደርጋለሁ፤ የፈሩትንም አመጣባቸዋለሁ፤ በተጣራሁ ጊዜ የመለሰ፣ በተናገርሁ ጊዜ ያደመጠ ሰው የለምና። በፊቴ ክፉ ነገር አደረጉ፤ የሚያስከፋኝንም መረጡ።”