ፊልጵስዩስ 4:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በተሰሎንቄ በነበርሁበት ጊዜ እንኳ፣ በችግሬ ወቅት ደጋግማችሁ ርዳታ ልካችሁልኛልና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በተሰሎንቄ እንኳ ሳለሁ፥ ከአንድ ጊዜ በላይ የሚያስፈልገኝን ነገር ልካችሁልኝ ነበርና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በተሰሎንቄም ችግር እንደ ደረሰብኝ ዐውቃችሁ መላልሳችሁ ርዳታ ልካችሁልኛል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በተሰሎንቄም ሳለሁ ደግሞ፥ አንድ ጊዜና ሁለት ጊዜ ለችግሬ ላካችሁልኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በተሰሎንቄ እንኳ ሳለሁ፥ አንድ ጊዜና ሁለት ጊዜ ያስፈለገኝን ሰዳችሁልኝ ነበርና። |
ወንድሞች ሆይ፤ ጥረታችንንና ድካማችንን ታስታውሳላችሁ፤ በማንም ላይ ሸክም እንዳንሆን ሌሊትና ቀን እየሠራን የእግዚአብሔርን ወንጌል ሰበክንላችሁ።
ከእኛ ወገን የሆኑት ለዕለት የሚያስፈልጋቸውን እንዲያገኙና ኑሯቸውም ፍሬ የሌለው እንዳይሆን ለመልካም ሥራ መትጋትን ይማሩ ዘንድ ይገባቸዋል።