ነህምያ 9:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እነርሱና አባቶቻችን ግን ትምክሕተኞችና ዐንገተ ደንዳኖች ሆኑ፤ ትእዛዞችህንም አልፈጸሙም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እነርሱና አባቶቻችን ግን ታበዩ፥ አንገታቸውን አደነደኑ፥ ትእዛዞችህንም አልሰሙም፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን የቀድሞ አባቶቻችን ትዕቢተኞችና እልኸኞች ሆኑ፤ ትእዛዞችህንም አልጠበቁም፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ነገር ግን እነርሱና አባቶቻችን ታበዩ፤ አንገታቸውንም አደነደኑ፤ ትእዛዝህንም አልሰሙም፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን እነርሱና አባቶቻችን ታበዩ፥ አንገታቸውንም አደነደኑ፥ ትእዛዝህንም አልሰሙም፥ |
አባቶቻችን ታማኞች አልነበሩም፣ በአምላካችን በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ድርጊት ፈጸሙ፤ ተዉትም። ከእግዚአብሔር ማደሪያ ፊታቸውን መለሱ፤ ጀርባቸውንም አዞሩበት።
እንደ አባቶቻችሁም ዐንገተ ደንዳኖች አትሁኑ፤ ለእግዚአብሔር ተገዙ፤ እርሱ ለዘላለም ወደ ቀደሰውም መቅደስ ኑ። አስፈሪ ቍጣው ከእናንተ እንዲመለስም፣ እግዚአብሔር አምላካችሁን አገልግሉ።
እንደዚሁም በእግዚአብሔር ስም አምሎት በነበረው በንጉሥ ናቡከደነፆር ላይ ዐመፀ፤ ዐንገቱን አደነደነ፤ ልቡንም አጠነከረ እንጂ ወደ እስራኤል አምላክ ወደ እግዚአብሔር አልተመለሰም።
ታምራታዊ ምልክቶችንና ድንቆችን በፈርዖንና፣ በሹማምቱ ሁሉ፣ በምድሩም ሕዝብ ሁሉ ላይ ላክህ፤ ይህንም ያደረግኸው ግብጻውያን እንዴት በእብሪት እንዳስጨነቋቸው ስላወቅህ ነው። እስከ ዛሬም የሚጠራ ስም ለራስህ እንዲኖርህ አደረግህ።
“ወደ ሕግህ እንዲመለሱ አስጠነቀቅሃቸው፤ እነርሱ ግን እብሪተኞች ሆኑ። ትእዛዞችህንም አልፈጸሙም፤ ‘አንድ ሰው ቢፈጽማቸው በሕይወት የሚኖርባቸውን’ ሥርዐቶችህን ተላለፉ። እንቢተኞች ሆነው ጀርባቸውን አዞሩብህ፤ ዐንገታቸውን አደነደኑ፤ መስማትም አልፈለጉም።
እርሱም አለ፤ “የአምላካችሁን እግዚአብሔር ድምፅ በጥንቃቄ ብትሰሙ፣ በፊቱም ትክክል የሆነውን ብትፈጽሙ፣ ትእዛዞቹን ልብ ብትሉና ሥርዐቱንም ሁሉ ብትጠብቁ፣ በግብጻውያን ላይ ያመጣሁባቸውን ማንኛውንም ዐይነት በሽታ በእናንተ ላይ አላመጣም፤ ፈዋሻችሁ እኔ እግዚአብሔር ነኝና።”
“የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘እነሆ ዐንገታቸውን በማደንደን ቃሌን ስላልሰሙ በዚህች ከተማና በዙሪያዋ ባሉ መንደሮች ሁሉ ላይ ላደርስ ያሰብሁትን ጥፋት ሁሉ አመጣለሁ።’ ”
“የዚህ ትውልድ ሰዎች ሆይ፤ የእግዚአብሔርን ቃል አስተውሉ፤ “እኔ ለእስራኤል ሕዝብ ምድረ በዳ፣ ወይስ ድቅድቅ ጨለማ ያለበት ምድር ሆንሁበትን? ሕዝቤ፣ ‘እንደ ልባችን ልንሆን እንፈልጋለን፤ ተመልሰንም ወደ አንተ አንመጣም’ ለምን ይላል?
የቱን ያህል ዐመፀኞችና ዐንገተ ደንዳኖች እንደ ሆናችሁ ዐውቃለሁና። እኔ በሕይወት ከእናንተ ጋራ እያለሁ በእግዚአብሔር ላይ ካመፃችሁ፣ ከሞትሁ በኋላማ የቱን ያህል ልታምፁ!
ታዲያ ለእነርሱም ሆነ ለልጆቻቸው ለዘላለም መልካም እንዲሆንላቸው፣ እኔን እንዲፈሩና ሁልጊዜ ትእዛዞቼን ሁሉ እንዲጠብቁ እንደዚህ ያለ ልብ ቢኖራቸው ምናለ!
ስለዚህ አምላክህ እግዚአብሔር ይህችን መልካም ምድር እንድትወርሳት የሚሰጥህ ከጽድቅህ የተነሣ አለመሆኑን አስተውል፤ አንተ ዐንገተ ደንዳና ነህና።