ንጉሡም የይሁዳን ሰዎች ሁሉ፣ የኢየሩሳሌምን ከተማ ነዋሪዎች በሙሉ፣ ካህናቱንና ነቢያቱን ሁሉ ከልጅ እስከ ዐዋቂ አንድም ሰው ሳይቀር ይዞ ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ወጣ። በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የተገኘውንም የኪዳኑን መጽሐፍ ቃል በሙሉ በጆሯቸው እንዲሰሙት አነበበላቸው።
ነህምያ 8:1 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕዝቡ ሁሉ ከውሃ በር ፊት ለፊት በሚገኘው አደባባይ ላይ እንደ አንድ ሰው ተሰበሰቡ፤ ከዚያም እግዚአብሔር ለእስራኤል ያዘዘውን የሙሴ ሕግ መጽሐፍ እንዲያመጣ ለጸሓፊው ለዕዝራ ነገሩት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕዝቡም ሁሉ በውኃው በር ፊት ወዳለው አደባባይ እንደ አንድ ሰው ሆነው ተሰበሰቡ፤ ጌታ ለእስራኤል ያዘዘውን የሙሴን ሕግ መጽሐፍ እንዲያመጣ ለጸሐፊው ለዕዝራ ነገሩት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእስራኤል ሕዝብ በሰባተኛው ወር በየከተሞቻቸው መስፈራቸውን አበቁ፤ በዚያም ወር በመጀመሪያው ቀን በኢየሩሳሌም የውሃ በር ተብሎ በሚጠራው አደባባይ በውስጥ በኩል ሕዝቡ ሁሉ በአንድነት ተሰበሰቡ፤ እነርሱም የሕግ ምሁሩን ዕዝራን እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት ለእስራኤል ሕዝብ የሰጠውን የኦሪትን ሕግ መጽሐፍ ያመጣላቸው ዘንድ ለመኑት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰባተኛውም ወር በደረሰ ጊዜ የእስራኤል ልጆች በከተሞቻቸው ነበሩ። ሕዝቡም ሁሉ በውኃው በር ፊት ወዳለው አደባባይ እንደ አንድ ሰው ሆነው ተሰበሰቡ፤ እግዚአብሔርም ለእስራኤል ያዘዘውን የሙሴን ሕግ መጽሐፍ ያመጣ ዘንድ ጸሓፊውን ዕዝራን ነገሩት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰባተኛውም ወር በደረሰ ጊዜ የእስራኤል ልጆች በከተሞቻቸው ነበሩ። ሕዝቡም ሁሉ በውኃው በር ፊት ወዳለው አደባባይ እንደ አንድ ሰው ሆነው ተሰበሰቡ፥ እግዚአብሔርም ለእስራኤል ያዘዘውን የሙሴን ሕግ መጽሐፍ ያመጣ ዘንድ ጸሐፊውን ዕዝራን ተናገሩት። |
ንጉሡም የይሁዳን ሰዎች ሁሉ፣ የኢየሩሳሌምን ከተማ ነዋሪዎች በሙሉ፣ ካህናቱንና ነቢያቱን ሁሉ ከልጅ እስከ ዐዋቂ አንድም ሰው ሳይቀር ይዞ ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ወጣ። በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የተገኘውንም የኪዳኑን መጽሐፍ ቃል በሙሉ በጆሯቸው እንዲሰሙት አነበበላቸው።
ንጉሡም የይሁዳን ሰዎች ሁሉ፣ የኢየሩሳሌምን ከተማ ነዋሪዎች በሙሉ፣ ካህናቱንና ሌዋውያንን ሁሉ ከልጅ እስከ ዐዋቂ አንድም ሰው ሳይቀር ይዞ ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ወጣ። በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የተገኘውንም የኪዳኑን መጽሐፍ ቃል በሙሉ በጆሯቸው እንዲሰሙት አነበበላቸው።
እግዚአብሔር ለእስራኤል የሰጠውን ሕግና ትእዛዝ ዐዋቂ ለነበረው ለካህኑና ለመምህሩ ዕዝራ ንጉሥ አርጤክስስ የሰጠው የደብዳቤ ቅጅ ይህ ነው፤
ይህ ዕዝራ ከባቢሎን መጣ፤ እርሱም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ለሙሴ የሰጠውን ሕግ በሚገባ የሚያውቅ የሕግ መምህር ነበር። የአምላኩ የእግዚአብሔር እጅ በርሱ ላይ ስለ ነበረች፣ የጠየቀውን ሁሉ ንጉሡ ፈቀደለት።
ከምንጭ በር ተነሥተው በቀጥታ ወደ ዳዊት ከተማ ደረጃዎች ወጡ፤ ከዚያም በቅጥሩ መውጫ በኩል አድርገው ከዳዊት ቤት በላይ በስተምሥራቅ ወደሚገኘው ወደ ውሃ በር ሄዱ።
በዖፌል ኰረብታ ላይ የሚኖሩት የቤተ መቅደሱ አገልጋዮች የውሃ በር ተብሎ ከሚጠራው ትይዩ ጀምሮ በስተምሥራቅ እስከሚገኘው ግንብ ድረስ መልሰው ሠሩ።
ስለዚህ ሕዝቡ ወጥተው ቅርንጫፎች አመጡ፤ እያንዳንዳቸውም በየቤታቸው ጣራ ሰገነት፣ በየግቢያቸው፣ በእግዚአብሔር ቤት አደባባይ፣ “በውሃ በር” አደባባይና በኤፍሬም በር አደባባይ ላይ ዳስ ሠሩ።
እርሱም በውሃ በር ትይዩ ወደሚገኘው አደባባይ ፊቱን አቅንቶ፣ በወንዶች፣ በሴቶችና በሚያስተውሉ ሰዎች ሁሉ ፊት በመቆም፣ ከማለዳ ጀምሮ እስከ ቀትር ድረስ ድምፁን ከፍ አድርጎ አነበበ፤ ሕዝቡም ሁሉ የሕጉን መጽሐፍ በጥሞና አደመጡ።
እርሱም፣ “ስለዚህም የመንግሥተ ሰማይን ምስጢር የተረዳ ማንኛውም የኦሪት ሕግ መምህር፣ ከከበረ ሀብቱ ክምችት አዲሱንም አሮጌውንም የሚያወጣ ባለንብረት ይመስላል” አላቸው።
“እናንተ ግብዞች የኦሪት ሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን ወዮላችሁ! ሰዎች ወደ መንግሥተ ሰማይ እንዳይገቡ በሩን ስለምትዘጉባቸው እናንተ ራሳችሁ አትገቡም፤ መግባት የሚፈልጉትንም አታስገቡም። [
ስለዚህ ነቢያትን፣ ጠቢባንንና መምህራንን እልክላችኋለሁ፤ ከነዚህም አንዳንዶቹን ትገድላላችሁ፤ አንዳንዶቹን ትሰቅላላችሁ፤ ሌሎቹንም በምኵራቦቻችሁ ትገርፏቸዋላችሁ፤ ከከተማ ወደ ከተማ ታሳድዷቸዋላችሁ።
ከዚያም ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ያሉ እንዲሁም በገለዓድ ምድር የሚገኙ እስራኤላውያን ሁሉ እንደ አንድ ሰው ሆነው ወጡ፤ በምጽጳም በእግዚአብሔር ፊት ተሰበሰቡ።
ከዚያም ሕዝቡ እንደ አንድ ሰው ሆነው በመነሣት እንዲህ አሉ፤ “ከእኛ ማንም ሰው ወደ ድንኳኑ አይሄድም፤ ማንኛችንም ወደ ቤታችን አንመለስም።