ስለ አንተም ‘በአይሁድ ንጉሥ አለ’ ብለው በኢየሩሳሌም የሚያውጁ ነቢያትን እንኳ ሳይቀር እንደ ሾምህ ተወርቷል፤ ይህም ነገር ለንጉሡ መድረሱ አይቀርም፤ ስለዚህ መጥተህ በአንድነት እንመካከር።”
ነህምያ 6:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔም “አንተ የምትለውን የመሰለ ምንም ነገር አልተደረገም፤ ይህ አንተ በአእምሮህ የፈጠርኸው ነው” ብዬ መልስ ላክሁበት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔም እንዲህ ብዬ ላክሁበት፦ “አንተ ከምትለው ነገር አንድም አልተደረገም፥ አንተ ከልብህ ፈጥረኸዋልና” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔም “ይህ የምትለው ነገር ሁሉ ምንም እውነትነት የሌለውና አንተ ራስህ የፈለሰፍከው ሐሰት ነው” ብዬ መለስኩለት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔም፥ “አንተ ከልብህ ፈጥረኸዋል እንጂ እንደ ተናገርኸው ነገር አይደለም” ብዬ ላክሁበት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔም፦ አንተ ከልብህ ፈጥረኸዋል እንጂ እንደ ተናገርኸው ነገር ምንም የለም ብዬ ላክሁበት። |
ስለ አንተም ‘በአይሁድ ንጉሥ አለ’ ብለው በኢየሩሳሌም የሚያውጁ ነቢያትን እንኳ ሳይቀር እንደ ሾምህ ተወርቷል፤ ይህም ነገር ለንጉሡ መድረሱ አይቀርም፤ ስለዚህ መጥተህ በአንድነት እንመካከር።”
ፍትሕን የሚጠራ ማንም የለም፤ ጕዳዩን በቅንነት የሚያቀርብ የለም፤ በከንቱ ነገር ታመኑ፤ ሐሰትን ተናገሩ፤ ሁከትን ፀነሱ፤ ክፋትንም ወለዱ።
ልባቸው ወደ ክፋት ያዘነበለው ሁለቱ ነገሥታት፣ በአንድ ገበታ ዐብረው ይቀመጣሉ፤ እርስ በርሳቸውም ሐሰትን ይነጋገራሉ፤ ነገር ግን የተወሰነው ጊዜ ገና ስለ ሆነ አይከናወንላቸውም።
እናንተ የአባታችሁ የዲያብሎስ ናችሁ፤ የአባታችሁንም ፍላጎት ለመፈጸም ትሻላችሁ። እርሱ ከመጀመሪያ ነፍሰ ገዳይ ነበር፤ በርሱ ዘንድ እውነት ስለሌለ በእውነት አልጸናም፤ እርሱ ሐሰተኛ፣ የሐሰትም አባት በመሆኑ ሐሰትን ሲናገር፣ የሚናገረው ከራሱ አፍልቆ ነው፤
ጳውሎስም እንዲህ አለ፤ “አሁንም ቢሆን ፍትሕ ማግኘት በምችልበት፣ በቄሳር ፍርድ ወንበር ፊት ቆሜአለሁ፤ አንተ ራስህ በሚገባ እንደምታውቀው በአይሁድ ላይ ምንም በደል አልፈጸምሁም፤