ነህምያ 3:23 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእነርሱ ቀጥሎ ብንያምና አሱብ ከቤታቸው ፊት ለፊት ያለውን መልሰው ሠሩ፤ ከእነርሱም ቀጥሎ የሐናንያ ልጅ የመዕሤያ ልጅ ዓዛርያስ በቤቱ አጠገብ ያለውን መልሶ ሠራ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእነርሱም በኋላ ብንያምና ሐሹብ ከቤታቸው ፊት ለፊት ያለውን አደሱ። ከእነርሱም በኋላ የአናንያ ልጅ የማዓሤያ ልጅ አዛርያ በቤቱ አጠገብ ያለውን አደሰ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእነርሱም ቀጥሎ ብንያምና ሐሹብ በመኖሪያ ቤቶቻቸው ፊት ለፊት ያለውን ክፍል ሠሩ። የዐናኒያ የልጅ ልጅ የሆነውም የመዕሤያ ልጅ ዐዛርያ በራሱ መኖሪያ ቤት አጠገብ ያለውን ክፍል ሠራ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእነርሱም በኋላ ብንያምና አሴብ በቤታቸው አንጻር ያለውን ሠሩ። ከእነርሱም በኋላ የሐናንያ ልጅ የመዓስያ ልጅ ዓዛርያስ በቤቱ አጠገብ ያለውን ሠራ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእነርሱም በኋላ ብንያምና አሱብ በቤታቸው አንጻር ያለውን አደሱ። ከእነርሱም በኋላ የሐናንያ ልጅ የመዕሤያ ልጅ ዓዛርያስ በቤቱ አጠገብ ያለውን አደሰ። |
ጸሓፊው ዕዝራ ለዚሁ ተብሎ በተሠራውና ከፍ ብሎ በሚገኘው የዕንጨት መድረክ ላይ ቆሞ ነበር፤ በአጠገቡም በስተ ቀኙ በኩል መቲትያ፣ ሽማዕ፣ ዓናያ፣ ኦርዮ፣ ኬልቅያስ፣ መዕሤያ፣ በስተ ግራው በኩል ደግሞ ፈዳያ፣ ሚሳኤል፣ መልክያ፣ ሐሱም፣ ሐሽበዳና፣ ዘካርያስና ሜሱላም ቆመው ነበር።
ሌዋውያኑ ኢያሱ፣ ባኒ፣ ሰራብያ፣ ያሚን፣ ዓቁብ፣ ሳባታይ፣ ሆዲያ፣ መዕሤያ፣ ቆሊጣስ፣ ዓዛርያስ፣ ዮዛባት፣ ሐናን፣ ፌልያ ሕዝቡ በዚያው ቆመው እንዳሉ ሕጉን አስረዷቸው።