ነህምያ 3:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የኢየሩሳሌም አውራጃ እኩሌታ ገዥ የሆነው የአሎኤስ ልጅ ሰሎም ከሴት ልጆቹ ጋራ በመሆን ቀጥሎ ያለውን ክፍል መልሶ ሠራ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአጠገባቸውም እሱና ሴት ልጆቹ የኢየሩሳሌም ግዛት እኩሌታ ገዢ የሆነው የሃሎሔሽ ልጅ ሻሉም አደሰ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀጥሎ ያለውንም ክፍል የሌላው የኢየሩሳሌም ወረዳ እኩሌታ ገዢ የሆነው የሀሎሔሽ ልጅ ሻሉም ሠራ፤ ሴቶች ልጆቹም ሥራውን ይረዱት ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአጠገባቸውም የኢየሩሳሌም ግዛት እኩሌታ ገዢ የአሎኤስ ልጅ ሰሎምና ሴቶች ልጆቹ ሠሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአጠገባቸውም የኢየሩሳሌም ግዛት እኩሌታና የመንደሮችዋ አለቃ የአሎኤስ ልጅ ሰሎም አደሰ። |
አዎን፤ አንተ ታማኝ ባልደረባዬ ሆይ፤ ወንጌልን በማሠራጨት ረገድ ከእኔና ከቀሌምንጦስ ጋራ እንዲሁም ስማቸው በሕይወት መጽሐፍ ከተጻፉት ከሌሎች የሥራ ጓደኞቼ ጋራ የተጋደሉትን እነዚህን ሴቶች እንድትረዳቸው እለምንሃለሁ።