በዚያም ቀን የሙሴን መጽሐፍ ከፍ ባለ ድምፅ ለሕዝቡ አነበቡ፤ አሞናዊም ሆነ ሞዓባዊ ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ ፈጽሞ እንዳይገባ የሚከለክል ተጽፎ ተገኘ፤
ነህምያ 2:10 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሖሮናዊው ሰንባላጥና አሞናዊው ሹም ጦቢያ ይህን በሰሙ ጊዜ፣ ስለ እስራኤላውያን ደኅንነት የሚቈረቈር ሰው በመምጣቱ እጅግ ተበሳጩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሖሮናዊው ሳንባላጥና አገልጋይ የሆነው አሞናዊው ጦብያ ለእስራኤል ልጆች መልካምን ነገር የሚሻ ሰው እንደመጣ በሰሙ ጊዜ እጅግ ተበሳጩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን የቤትሖሮን ከተማ ነዋሪ የሆነው ሰንባላጥና የዐሞን ክፍለ ሀገር ባለሥልጣን የሆነው ጦቢያ ለእስራኤል ሕዝብ ደኅንነት መልካም ነገር የሚሠራ ሰው መምጣቱን ሰምተው እጅግ ተቈጡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሖሮናዊውም ሰንባላጥና አገልጋዩ አሞናዊው ጦብያ ለእስራኤል ልጆች መልካምን ነገር የሚሻ ሰው እንደ መጣ በሰሙ ጊዜ እጅግ ተበሳጩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሖሮናዊውም ሰንባላጥና ባሪያው አሞናዊ ጦብያ ለእስራኤል ልጆች መልካምን ነገር የሚሻ ሰው እንደ መጣ በሰሙ ጊዜ እጅግ ተበሳጩ። |
በዚያም ቀን የሙሴን መጽሐፍ ከፍ ባለ ድምፅ ለሕዝቡ አነበቡ፤ አሞናዊም ሆነ ሞዓባዊ ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ ፈጽሞ እንዳይገባ የሚከለክል ተጽፎ ተገኘ፤
ነገር ግን ሖሮናዊው ሰንባላጥ፣ አሞናዊው ሹም ጦቢያና ዐረባዊው ጌሳም ይህን ሲሰሙ አፌዙብን፤ አንቋሸሹንም፤ እንዲሁም፣ “የምታደርጉት ይህ ምንድን ነው? በንጉሡ ላይ ልታምፁ ትፈልጋላችሁን?” አሉ።
ሰንባላጥ፣ ጦቢያ፣ ዐረቦች፣ የአሞንና የአሽዶድ ሰዎች፣ የኢየሩሳሌም ቅጥር ሥራ እየተፋጠነና ክፍት ቦታዎቹም ሁሉ እየተሞሉ መሆናቸውን በሰሙ ጊዜ እጅግ ተቈጡ።
እስከዚያች ጊዜ ድረስ ለበሮቹ መዝጊያ ባልገጥምላቸውም እንኳ፣ ቅጥሩን መሥራቴንና የቀረ ክፍት ቦታ አለመኖሩን ሰንባላጥ፣ ጦቢያ፣ ዐረባዊው ጌሳምና የቀሩትም ጠላቶቻችን በሰሙ ጊዜ፣
ጠላቶቻችን ሁሉ ይህን ሲሰሙ፣ በዙሪያችን ያሉ አሕዛብ ሁሉ ፈሩ፤ በራሳቸው መተማመንም አልቻሉም፤ ምክንያቱም ይህ ሥራ የተከናወነው በአምላካችን ርዳታ መሆኑን ተገንዝበዋል።
አይሁዳዊው መርዶክዮስ በማዕርግ ከንጉሡ ከጠረክሲስ ቀጥሎ ሁለተኛ፣ ከአይሁድ መካከልም ቀዳሚውን ስፍራ የያዘ ሰው ነበር፤ ለወገኖቹ መልካም በማድረጉና ለአይሁድም ሁሉ ደኅንነት የቆመ በመሆኑ፣ በብዙዎቹ አይሁድ ወገኖቹ ዘንድ እጅግ የተከበረ ነበር።
ልቤ ስለ ሞዓብ አለቀሰ፤ ስደተኞቿም እስከ ዞዓር፣ እስከ ዔግላት ሺሊሺያ ሸሹ፤ እንባቸውን እያፈሰሱ ወደ ሉሒት ወጡ፤ በሖሮናይም መንገድም፣ ስለ ጥፋታቸው ዋይ እያሉ ነጐዱ።
እስማኤል በምጽጳ የቀረውን ሕዝብ ሁሉ ምርኮኛ አደረገ፤ እነርሱም የባቢሎን የክብር ዘበኞች አዛዥ ናቡዘረዳን የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን በላያቸው ገዥ አድርጎ የሾመባቸው የንጉሡ ሴቶች ልጆችና በዚያ የቀሩት ሌሎች ሰዎች ሁሉ ነበሩ። የናታንያ ልጅ እስማኤል እነዚህን ማርኮ ወደ አሞናውያን ለመሻገር ተነሣ።
“ከሐሴቦን እስከ ኤልያሊና እስከ ያሀጽ፣ ከዞዓር እስከ ሖሮናይም፣ እስከ ዔግላት ሺሊሺያ ድረስ፣ ጩኸታቸው ከፍ ብሎ ይሰማል፤ የኔምሬም ውሃ እንኳ ደርቋልና።