La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ነህምያ 13:7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ወደ ኢየሩሳሌም ተመለስሁ፤ በዚያም ኤልያሴብ በእግዚአብሔር ቤት አደባባይ ለጦቢያ አንድ መኖሪያ ክፍል በመስጠት የፈጸመውን ክፉ ድርጊት ተረዳሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ወደ ኢየሩሳሌምም መጣሁ፥ ኤልያሺብ በእግዚአብሔር ቤት አደባባይ ለጦብያ ጓዳውን በማዘጋጀት ያደረገውን ክፉ ነገር አስተዋልሁ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ወደ ኢየሩሳሌም ተመለስኩ፤ እዚያም እንደ ደረስኩ ኤልያሺብ ለጦቢያ በቤተ መቅደሱ ግቢ ውስጥ አንድ መኖሪያ ክፍል የፈቀደለት መሆኑን ሰማሁ፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም መጣሁ፤ ኤል​ያ​ሴ​ብም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አደ​ባ​ባይ ለጦ​ቢያ ዕቃ ቤቱን በማ​ዘ​ጋ​ጀት ያደ​ረ​ገ​ውን ክፉ ነገር አስ​ተ​ዋ​ልሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ወደ ኢየሩሳሌምም መጣሁ፥ ኤልያሴብም በእግዚአብሔር ቤት አደባባይ ለጦብያ ጓዳውን በማዘጋጀት ያደረገውን ክፉ ነገር አስተዋልሁ።

Ver Capítulo



ነህምያ 13:7
8 Referencias Cruzadas  

የኤልዮዔናይም ወንዶች ልጆች፤ ሆዳይዋ፣ ኤልያሴብ፣ ፌልያ፣ ዓቁብ፣ ዮሐናን፣ ደላያ፣ ዓናኒ፤ በአጠቃላይ ሰባት ናቸው።


እነዚህ ነገሮች ከተፈጸሙ በኋላ መሪዎቹ ወደ እኔ መጥተው እንዲህ አሉኝ፤ “ካህናቱንና ሌዋውያኑን ጨምሮ የእስራኤል ሕዝብ ከጎረቤቶቻቸው ከከነዓናውያን፣ ከኬጢያውያን፣ ከፌርዛውያን፣ ከኢያቡሳውያን፣ ከአሞናውያን፣ ከሞዓባውያን፣ ከግብጻውያንና ከአሞራውያን ርኩሰት ራሳቸውን አልለዩም።


በዚያም ቀን የሙሴን መጽሐፍ ከፍ ባለ ድምፅ ለሕዝቡ አነበቡ፤ አሞናዊም ሆነ ሞዓባዊ ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ ፈጽሞ እንዳይገባ የሚከለክል ተጽፎ ተገኘ፤


ከዚህ በፊት የእህል ቍርባኑ፣ ዕጣኑ፣ የቤተ መቅደሱ ዕቃዎች፣ የእህሉ ዐሥራትና፣ ለሌዋውያን፣ ለመዘምራንና ለበር ጠባቂዎች የታዘዘው አዲሱ ወይንና ዘይት፣ ለካህናቱም የሚመጣው ስጦታ ይቀመጥበት የነበረውን ትልቁን የዕቃ ቤት እንዲኖርበት ሰጥቶት ነበር።


ዮድ በሀብቷ ሁሉ ላይ፣ ጠላት እጁን ዘረጋ፤ ወደ ጉባኤህ እንዳይገቡ የከለከልሃቸው፣ ጣዖት የሚያመልኩ አሕዛብ፣ ወደ መቅደሷ ሲገቡ አየች።


ወንድሞች ሆይ፤ በመካከላችሁ ክርክር እንዳለ ከቀሎዔ ቤተ ሰብ ሰምቻለሁ፤