የእስራኤል ሕዝብና ሌዋውያኑ ጭምር፣ ከእህሉ፣ ከአዲሱ ወይን ጠጅና ከዘይቱ ያዋጡትን፣ የመቅደሱ ዕቃዎች ወደሚቀመጡባቸው፣ አገልጋይ ካህናት፣ በር ጠባቂዎቹና መዘምራኑ ወደሚያርፉባቸው ዕቃ ቤቶች ያምጡ። “እኛም የአምላካችንን ቤት ቸል አንልም።”
ነህምያ 13:11 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ሹማምቱን ገሥጬ፣ “ቤተ መቅደሱ እስከዚህ ቸል የተባለው ለምንድን ነው?” ብዬ ጠየቅኋቸው። ከዚያም እነርሱን በአንድነት ሰብስቤ ወደ ምድብ ሥራቸው እንዲመለሱ አደረግሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔም፦ የእግዚአብሔር ቤት ስለምን ተተወ? ብዬ ከአለቆቹ ጋር ተከራከርሁ። ሰበሰብኋቸውም፥ በየስፍራቸውም አቆምኋቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቤተ መቅደሱም ይህን ያኽል ቸል እስኪባል ዝም ብለው በመመልከታቸው ባለሥልጣኖችን ገሠጽኩ፤ ሌዋውያኑንና መዘምራኑንም ወደ ቤተ መቅደስ መልሼ በማምጣት ሥራቸውን እንዲቀጥሉ አደረግሁ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔም፥ “የእግዚአብሔር ቤት ስለ ምን ተተወ?” ብዬ ከአለቆቹ ጋር ተከራከርሁ። ሰበሰብኋቸውም፤ በየስፍራቸውም አቆምኋቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔም፦ የእግዚአብሔር ቤት ስለ ምን ተተወ? ብዬ ከአለቆቹ ጋር ተከራከርሁ። ሰበሰብኋቸውም፥ በየስፍራቸውም አቆምኋቸው። |
የእስራኤል ሕዝብና ሌዋውያኑ ጭምር፣ ከእህሉ፣ ከአዲሱ ወይን ጠጅና ከዘይቱ ያዋጡትን፣ የመቅደሱ ዕቃዎች ወደሚቀመጡባቸው፣ አገልጋይ ካህናት፣ በር ጠባቂዎቹና መዘምራኑ ወደሚያርፉባቸው ዕቃ ቤቶች ያምጡ። “እኛም የአምላካችንን ቤት ቸል አንልም።”
እኔም ገሠጽኋቸው፤ ርግማንም አወረድሁባቸው። አንዳንዶቹን መታኋቸው፤ ጠጕራቸውንም ነጨሁ። በእግዚአብሔር ስም እንዲህ ስል አማልኋቸው፤ “ሴቶች ልጆቻችሁን ለወንዶች ልጆቻቸው አትስጡ፤ ሴቶች ልጆቻቸውንም ለወንዶች ልጆቻችሁ አትውሰዱ።