እስራኤል ሁሉ በየትውልድ ሐረጋቸው ተቈጥረው ስማቸው በእስራኤል ነገሥታት መዝገብ ላይ ሰፈረ። የይሁዳ ሕዝብ ከፈጸሙት በደል የተነሣ ተማርከው ወደ ባቢሎን ተወሰዱ።
ነህምያ 11:11 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔር ቤት አለቃ የአኪጦብ ልጅ፣ የመራዮት ልጅ፣ የሳዶቅ ልጅ፣ የሜሱላም ልጅ፣ የኬልቅያስ ልጅ ሠራያ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእግዚአብሔር ቤት አለቃ የአሒጡብ ልጅ የምራዮት ልጅ፥ የጻዶቅ ልጅ የምሹላም ልጅ፥ የሒልቂያ ልጅ ሥራያ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሠራያ፥ የሒልቅያ ልጅ፥ የመሹላም ልጅ፥ የጻዶቅ ልጅ፥ የመራዮት ልጅ፥ የእግዚአብሔር ቤት አለቃ የነበረው የአሒጡብ ልጅ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔርም ቤት አለቃ የአኪጦብ ልጅ፥ የማርዮት ልጅ፥ የሳዶቅ ልጅ፥ የሜሱላም ልጅ፥ የኬልቅያስ ልጅ ሣርያ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔርም ቤት አለቃ የአኪጦብ ልጅ የመራዮት ልጅ የሳዶቅ ልጅ የሜሱላም ልጅ የኪልቅያስ ልጅ ሠራያ፥ |
እስራኤል ሁሉ በየትውልድ ሐረጋቸው ተቈጥረው ስማቸው በእስራኤል ነገሥታት መዝገብ ላይ ሰፈረ። የይሁዳ ሕዝብ ከፈጸሙት በደል የተነሣ ተማርከው ወደ ባቢሎን ተወሰዱ።
“የእግዚአብሔር በሆነው ነገር ሁሉ ላይ የካህናቱ አለቃ አማርያ፣ የንጉሡ በሆነው ነገር ሁሉ ላይ የይሁዳ ነገድ መሪ የሆነው የእስማኤል ልጅ ዝባድያ በላያችሁ ተሾመዋል፤ ሌዋውያኑ ደግሞ በፊታችሁ አለቆች ሆነው ያገለግላሉ፤ በርትታችሁ ሥሩ፤ እግዚአብሔርም መልካም ከሚያደርጉ ጋራ ይሁን።”
ይሒኤል፣ ዓዛዝያ፣ ናሖት፣ አሣሄል፣ ይሬሞት፣ ዮዛባት፣ ኤሊኤል፣ ሰማኪያ፣ መሐትና በናያስ በንጉሡ ሕዝቅያስና በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ኀላፊ በዓዛርያስ ተሹመው በኮናንያና በወንድሙ በሰሜኢ ሥር ሆነው ተቈጣጣሪዎች ነበሩ።
የቤተ መቅደሱን ሥራ ያከናወኑት ወንድሞቻቸው፣ 822 ሰዎች፤ የመልክያ ልጅ፣ የፋስኮር ልጅ፣ የዘካርያስ ልጅ፣ የአማሲ ልጅ፣ የፈላልያ ልጅ፣ የይሮሐም ልጅ ዓዳያ፤