ሰውንም ካስወጣው በኋላ፣ ወደ ሕይወት ዛፍ የሚወስደውን መንገድ ለመጠበቅ ኪሩቤልንና በየአቅጣጫው የምትገለባበጥ ነበልባላዊ ሰይፍ ከዔድን በስተምሥራቅ አኖረ።
ናሆም 3:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፈረሰኛው ይጋልባል፤ ሰይፍ ይንቦገቦጋል፤ ጦር ያብረቀርቃል። የሞተው ብዙ ነው፤ ሬሳ በሬሳ ሆኗል፤ ስፍር ቍጥር የለውም፤ መተላለፊያ አልተገኘም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፈረሰኛው ይጋልባል፥ ሰይፍ ይንቦገቦጋል፥ ጦር ይብለጨለጫል የተገደለ ብዛት፥ የበድን ክምር፥ ሬሳው ማለቂያ የለውም፤ በሬሳቸውም ይሰናከላሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፈረሰኞች ወደፊት እየገፉ የሚያብረቀርቅ ሰይፋቸውንና የሚያብለጨልጭ ጦራቸውን ያነሣሉ፤ ብዙ ሰዎች ስለ ተገደሉ ሬሳዎች ተከምረዋል፤ ከሬሳውም ብዛት የተነሣ በዚያ የሚያልፍ ሰው ሁሉ ይደናቀፋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፈረሰኛው ይጋልባል፥ ሰይፍም ይንቦገቦጋል፥ ጦርም ይብለጨለጫል፣ የተገደሉትም ይበዛሉ፥ በድኖችም በክምር ይከመራሉ፥ ሬሳቸውም አይቈጠርም፣ በሬሳቸውም ይሰናከላሉ። |
ሰውንም ካስወጣው በኋላ፣ ወደ ሕይወት ዛፍ የሚወስደውን መንገድ ለመጠበቅ ኪሩቤልንና በየአቅጣጫው የምትገለባበጥ ነበልባላዊ ሰይፍ ከዔድን በስተምሥራቅ አኖረ።
በዚያችም ሌሊት የእግዚአብሔር መልአክ ወጣ፤ ከአሦራውያን ሰፈር አንድ መቶ ሰማንያ ዐምስት ሺሕ ሰው ገደለ፤ ሰዎቹ ማለዳ ሲነሡ፤ ቦታው ሬሳ በሬሳ ነበር።
ከዚያም የእግዚአብሔር መልአክ ወጣ፤ ከአሦራውያን ሰፈር አንድ መቶ ሰማንያ ዐምስት ሺሕ ሰው ገደለ፤ ሰዎቹ ማለዳ ሲነሡ፤ ቦታው ሬሳ በሬሳ ነበር።
አንተና ወታደሮችህ ሁሉ፣ ከአንተም ጋራ ያሉ ሕዝቦች በእስራኤል ተራሮች ላይ ትወድቃላችሁ። ነጣቂ አሞሮችና የዱር አራዊት ይበሏችሁ ዘንድ አሳልፌ እሰጣችኋለሁ።