ሚክያስ 2:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነቢያቶቻቸው፣ “ትንቢት አትናገርብን፤ ስለ እነዚህ ነገሮች ትንቢት አትናገር፤ ውርደት አይደርስብንም” ይላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “አትስበኩ” ብለው ይሰብካሉ፤ “ስለ እነዚህ ነገሮች መስበክ የለባችሁም፤ ውርደት አይደርስብንም።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእነርሱ ነቢያት “ትንቢት አትናገር፤ እንደዚህ ያለው ውርደት የማይደርስብን ስለ ሆነ ስለ ነዚህ ጉዳዮች ትንቢት አትናገር” ይሉኛል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ትንቢት አትናገሩ ብለው ይናገራሉ፥ በእነዚህ ላይ ትንቢት አይናገሩም፥ ስድብም አይርቅም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ትንቢት አትናገሩ ብለው ይናገራሉ፥ በእነዚህ ላይ ትንቢት አይናገሩም፥ ስድብም አይርቅም። |
ባለራእዮችን፣ “ከእንግዲህ ራእይን አትዩ!” ይላሉ፤ ነቢያትንም እንዲህ ይላሉ፤ “እውነተኛውን ትንቢት ከእንግዲህ አትንገሩን፤ ደስ የሚያሠኘውን ንገሩን፤ የሚያማልለውን ተንብዩልን።
የዖምሪን ሥርዐት፣ የአክዓብን ቤት ልምድ ሁሉ የሙጥኝ ብለሃል፤ ትውፊታቸውንም ተከትለሃል። ስለዚህ አንተን ለውድመት፣ ሕዝብህን ለመዘባበቻ አሳልፌ እሰጣለሁ፤ አሕዛብም ይሣለቁብሃል።”
ይሁን እንጂ፣ ይህ ነገር ከእንግዲህ በሕዝቡ መካከል ይበልጥ እንዳይስፋፋ፣ እነዚህም ሰዎች ዳግመኛ በዚህ ስም ለማንም እንዳይናገሩ እናስጠንቅቃቸው።”
“በዚህ ስም እንዳታስተምሩ በጥብቅ አስጠንቅቀናችሁ ነበር፤ እናንተ ግን ኢየሩሳሌምን በትምህርታችሁ ሞላችኋት፤ ደግሞም እኛን ለዚህ ሰው ደም ተጠያቂዎች ልታደርጉን ቈርጣችሁ ተነሣችሁ።”