ሚክያስ 1:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ምክንያት አለቅሳለሁ፤ ዋይ ዋይም እላለሁ፤ ባዶ እግሬንና ዕርቃኔን እሄዳለሁ፤ እንደ ቀበሮ አላዝናለሁ፤ እንደ ጕጕትም አቃስታለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚህ ምክንያት አለቅሳለሁ፥ ዋይ ዋይ እላለሁ፥ ባዶ እግሬንና ራቁቴን እሄዳለሁ፤ እንደ ቀበሮ አላዝናለሁ፥ እንደ ሰጎን ልጆችም የዋይታ ድምፅ አሰማለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ሚክያስ እንዲህ አለ፦ “በዚህ ምክንያት ‘ዋይ! ዋይ!’ እያልኩ አለቅሳለሁ፤ ሐዘኔንም ለመግለጥ ራቊቴንና ባዶ እግሬን እሄዳለሁ፤ እንደ ቀበሮ እጮኻለሁ፤ እንደ ሰጎንም የዋይታ ድምፅ አሰማለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ ነገር ዋይ ብላ ታለቅሳለች፥ ባዶ እግርዋንና ዕራቁትዋን ሆና ትሄዳለች፥ እንደ ቀበሮ ታለቅሳለች፥ እንደ ሰጐንም ዋይ ትላለች፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ ነገር ዋይ ብላ ታለቅሳለች፥ ባዶ እግርዋንና ዕራቁትዋን ሆና ትሄዳለች፥ እንደ ቀበሮ ታለቅሳለች፥ እንደ ሰጐንም ዋይ ትላለች፥ |
መርዶክዮስ የተደረገውን ሁሉ ባወቀ ጊዜ፣ ልብሱን ቀደደ፤ ከዚያም ማቅ ለብሶ፣ በራሱ ላይ ዐመድ ነስንሶ ድምፁን ከፍ በማድረግ አምርሮ እየጮኸ ወደ ከተማዪቱ መካከል ወጣ።
ነገር ግን የምድረ በዳ አራዊት በዚያ ይተኛሉ፤ ቀበሮዎች ቤቶቿን ይሞላሉ፤ ጕጕቶች በዚያ ይኖራሉ፤ በበረሓ ፍየል የሚመሰሉ አጋንንትም ይዛለሉበታል።
ስለዚህ ስለ ሴባማ የወይን ተክል፣ ኢያዜር እንዳለቀሰች፣ እኔም አለቅሳለሁ፤ ሐሴቦን ሆይ፤ ኤልያሊ ሆይ፤ በእንባዬ አርስሻለሁ! ፍሬ ባፈራሽበት ወቅት የነበረው ሆታ፣ መከርሽም ሲደርስ የነበረው ደስታ ተቋርጧልና።
እናንተ ትዕቢት የወጠራችሁ ሴቶች ተንቀጥቀጡ፤ እናንተ ተደላድላችሁ የምትኖሩ ሴቶች ልጆች፣ በፍርሀት ተርበትበቱ! ልብሳችሁን አውልቁ፤ ወገባችሁን በማቅ ታጠቁ።
ወይ አበሳዬ! ወይ አበሳዬ! ሥቃይ በሥቃይ ላይ ሆነብኝ፤ አወይ፣ የልቤ ጭንቀት! ልቤ ክፉኛ ይመታል፤ ዝም ማለት አልችልም፤ የመለከትን ድምፅ፣ የጦርነትንም ውካታ ሰምቻለሁና።
ስለ ተራሮች አለቅሳለሁ፤ ዋይ ዋይ እላለሁ፤ በምድረ በዳ ስላሉትም መሰማሪያዎች ዐዝናለሁ። ሰው የማያልፍባቸው ባድማ ሆነዋል፤ የከብቶች ጩኸት አይሰማም፤ የሰማይ ወፎች ሸሽተዋል፤ የዱር አራዊትም ጠፍተዋል።
እነሆ የዋይታ ድምፅ ከጽዮን ተሰምቷል፤ እንዲህም ይላል፤ ‘ምንኛ ወደቅን! ውርደታችንስ እንዴት ታላቅ ነው! ቤቶቻችን ፈራርሰዋልና፤ አገራችንን ጥለን እንሂድ።’ ”
“የሰው ልጅ ሆይ፤ ስለ ብዙው የግብጽ ሰራዊት አልቅስ፤ እርሷንና የኀያላንን ሕዝቦች ሴት ልጆች ወደ ጕድጓድ ከሚወርዱት ጋራ ከምድር በታች አውርዳቸው።
በዚያ ቀን ሰዎች ይሣለቁባችኋል፤ በሐዘን እንጕርጕሮ እንዲህ እያሉ ያፌዙባችኋል፤ ‘እኛ ፈጽሞ ጠፍተናል፤ የወገኔ ርስት ተከፋፍሏል። ከእኔ ነጥቆ ወስዶ፣ ዕርሻዎቻችንን ላሸነፉን አከፋፈለ።’ ”
እርሱም ልብሱን አውልቆ፣ በሳሙኤልም ፊት ደግሞ ትንቢት ተናገረ፤ በዚህ ሁኔታም ቀኑንና ሌሊቱን በሙሉ ዕራቍቱን ተጋደመ። ሕዝቡ፣ “ሳኦልም ደግሞ ከነቢያት እንደ አንዱ ሆኖ ተቈጠረ?” ያለው በዚህ ምክንያት ነው።