ስለዚህም ቤርሳቤህ የአዶንያስን ጕዳይ ልትነግረው ወደ ንጉሥ ሰሎሞን ሄደች፤ ንጉሡም ሊቀበላት ተነሣ፤ እጅ ከነሣትም በኋላ በዙፋኑ ላይ ተቀመጠ፤ ንጉሡም ለእናቱ ሌላ ዙፋን አስመጥቶ በቀኙ አስቀመጣት።
ማቴዎስ 25:33 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በጎቹን በቀኙ፣ ፍየሎቹን ግን በግራው ያቆማቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጎቹን በቀኙ ፍየሎቹን ደግሞ በግራው ያቆማቸዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጻድቃንን በቀኙ፥ ኃጢአተኞችን በግራው ያቆማቸዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በጎችን በቀኙ ፍየሎችንም በግራው ያቆማቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በጎችን በቀኙ ፍየሎችንም በግራው ያቆማቸዋል። |
ስለዚህም ቤርሳቤህ የአዶንያስን ጕዳይ ልትነግረው ወደ ንጉሥ ሰሎሞን ሄደች፤ ንጉሡም ሊቀበላት ተነሣ፤ እጅ ከነሣትም በኋላ በዙፋኑ ላይ ተቀመጠ፤ ንጉሡም ለእናቱ ሌላ ዙፋን አስመጥቶ በቀኙ አስቀመጣት።
እርሱ የእግዚአብሔር ክብር ነጸብራቅና የባሕርዩ ትክክለኛ ምሳሌ ሆኖ፣ በኀያል ቃሉ ሁሉን ደግፎ ይዟል። የኀጢአት መንጻት ካስገኘ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ።