ዘሌዋውያን 7:34 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእስራኤላውያን የኅብረት መሥዋዕት ላይ የተወዘወዘውን ፍርምባና የቀረበውን ወርች ወስጃለሁ፤ ለካህኑ ለአሮንና ለልጆቹም ከእስራኤላውያን የሚያገኙት መደበኛ ድርሻቸው እንዲሆን ሰጥቻቸዋለሁ።’ ” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሚወዘወዘውን ፍርምባና እንደ ቁርባን የሚቀርበውን ወርች ከእስራኤል ልጆች ከሰላም መሥዋዕታቸው ወስጄ፥ ለካህኑ ለአሮንና ለልጆቹም ለዘለዓለም ድርሻ እንዲሆን ከእስራኤል ልጆች ዘንድ እነርሱን ሰጥቼአቸዋለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእስራኤላውያን የአንድነት መሥዋዕት መካከል የተወዘወዘውን ፍርንባና የሚቀርበውን ወርች ከእስራኤላውያን እንደሚቀርብላቸው ቋሚ ድርሻ አድርጌ ለካህኑ ለአሮንና ለልጆቹ ሰጥቻቸዋለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፍርምባውንና የቀኝ ወርቹን ከእስራኤል ልጆች ከደኅንነት መሥዋዕታቸው ወስጄአለሁ፤ ለካህኑ ለአሮንና ለልጆቹም ለዘለዓለም ሕግ እንዲሆን ከእስራኤል ልጆች ዘንድ ሰጥቼአቸዋለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሚወዘወዘውን ፍርምባና የሚነሣውን ወርች ከእስራኤል ልጆች ከደኅንነት መሥዋዕታቸው ወስጄአለሁ፥ ለካህኑ ለአሮንና ለልጆቹም ለዘላለም እድል ፈንታ እንዲሆን ከእስራኤል ልጆች ዘንድ ሰጥቼአቸዋለሁ። |
የራስ ማሰሪያዎችንም አድርግላቸው፤ ከዚያም አሮንንና ወንዶች ልጆቹን መታጠቂያዎችን አስታጥቃቸው፤ ክህነት የዘላለም ሥርዐት ይሆንላቸዋል። “በዚህም መንገድ አሮንንና ወንዶች ልጆቹን ትክናቸዋለህ።
ከዚያም ካህኑ የሚወዘወዝ መሥዋዕት በማድረግ በእግዚአብሔር ፊት ይወዘውዛቸዋል፤ እነዚህም የተቀደሱ ናቸው። ከተወዘወዘው ፍርምባና ከቀረበው ወርች ጋራ የተቀደሱ የካህኑ ድርሻ ይሆናሉ። ከዚህ በኋላ ናዝራዊው የወይን ጠጅ መጠጣት ይችላል።
ከዚያም አሮን ሌዋውያኑን የእግዚአብሔርን አገልግሎት ለማከናወን ዝግጁ እንዲሆኑ ከእስራኤላውያን መካከል እንደሚወዘወዝ መሥዋዕት በእግዚአብሔር ፊት ያቅርባቸው።