ዘሌዋውያን 7:25 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለእግዚአብሔር በእሳት ከሚቀርብ እንስሳ ሥብ የሚበላ ማንኛውም ሰው ከሕዝቡ ይወገድ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለጌታ በእሳት ከሚያቀርበው ከእንስሳ ስብ የሚበላ ሰው ሁሉ፥ ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ ይጠፋ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሚቃጠል መሥዋዕት ሆኖ ለእግዚአብሔር የቀረበውን እንስሳ ስብ የሚበላ ሰው ከእግዚአብሔር ሕዝብ ይለይ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለእግዚአብሔር በእሳት ከሚቀርበው ከእንስሳ ስብ የሚበላ ሁሉ ያች የበላች ሰውነት ከሕዝብዋ ተለይታ ትጥፋ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለእግዚአብሔር በእሳት ከሚቀርበው ከእንስሳ ስብ የሚበላ ሁሉ፥ ያ የበላ ሰው ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ ይጠፋልና። |
ከዚያም ከእጃቸው ወስደህ ከሚቃጠለው መሥዋዕት ጋራ ለእግዚአብሔር መልካም መዐዛ እንዲሆን በመሠዊያው ላይ አቃጥለው፤ ይህም ለእግዚአብሔር በእሳት የሚቃጠል መሥዋዕት ነው።
ማንኛውም ሰው የሰውን ርኩሰት ወይም ርኩስ እንስሳን ወይም ማንኛውንም ርኩስ ነገር ቢነካና ለእግዚአብሔር ከቀረበው የኅብረት መሥዋዕት ሥጋ ቢበላ፣ ያ ሰው ፈጽሞ ከሕዝቡ ይወገድ።’ ”