የሰበሰቡትን በጎሞር በሰፈሩ ጊዜ፣ ብዙ የሰበሰበ አላተረፈም፤ ጥቂትም የሰበሰበ አልጐደለበትም፤ እያንዳንዱ የሰበሰበው የሚያስፈልገውን ያህል ሆነ።
ዘሌዋውያን 7:10 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ማንኛውም በዘይት የተለወሰ ወይም ደረቅ የእህል ቍርባን ለአሮን ልጆች ሁሉ እኩል ይሰጥ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዘይትም የተለወሰው ወይም የደረቀው የእህል ቁርባን በጠቅላላ ለአሮን ልጆች ሁሉ ይሆናል፤ እያንዳንዱም እንደሌላው ወንድሙ ይደርሰዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዘይት የተለወሰም ቢሆን ወይም ደረቅ ያልበሰለው የእህል መባ ግን ትውልዳቸው ከአሮን ወገን ለሆነው ካህናት ሁሉ ይሰጥ፤ እርሱንም እኩል ይካፈሉት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዘይትም የተለወሰው ወይም የደረቀው የእህል ቍርባን ሁሉ ለአሮን ልጆች ሁሉ ይሆናል፤ ለእያንዳንዱም እኩል ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዘይትም የተለወሰው ወይም የደረቀው የእህል ቍርባን ሁሉ ለአሮን ልጆች ሁሉ ይሆናል፤ ለሁሉም ይሆናል። |
የሰበሰቡትን በጎሞር በሰፈሩ ጊዜ፣ ብዙ የሰበሰበ አላተረፈም፤ ጥቂትም የሰበሰበ አልጐደለበትም፤ እያንዳንዱ የሰበሰበው የሚያስፈልገውን ያህል ሆነ።
በአሁኑ ጊዜ የእናንተ ትርፍ የእነርሱን ጕድለት ያሟላል፤ የእነርሱም ደግሞ በተራው የእናንተን ጕድለት ያሟላል፤ በዚህም ያላችሁን እኩል ትካፈላላችሁ።