እነዚህ ሁሉ ሚስቶቻቸውን ለመፍታት ቃል በመግባት እጃቸውን ሰጡ፤ ስለ በደላቸውም እያንዳንዳቸው ከመንጋው አንዳንድ አውራ በግ ለበደል መሥዋዕት አቀረቡ።
ዘሌዋውያን 6:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከመንጋውም እንከን የሌለበትን ዋጋው ተመጣጣኝ የሆነ አውራ በግ ስለ በደሉ መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር ለማቅረብ ወደ ካህኑ ያምጣ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ተመጣጣኝ የሆነ ዋጋ ለበደል መሥዋዕት፥ ከመንጋው ነውር የሌለበትን አውራ በግ፥ ለጌታ ስለ በደሉ መሥዋዕት ወደ ካህኑ ያመጣል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለበደሉም ማስተስረያ ምንም ነውር የሌለበት አንድ ተባዕት በግ ወይም በታወቀው ተመን የተተመነውን ገንዘብ መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር ያቅርብ፤ እርሱንም አምጥቶ ለካህኑ ይስጥ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለ በደል መሥዋዕትም ከመንጋው ነውር የሌለበትን፥ ዋጋው እንደ በደሉ የተገመተውን አውራ በግ ለእግዚአብሔር ያምጣ።። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለ በደል መሥዋዕትም ለእግዚአብሔር ከመንጋው ነውር የሌለበትን አውራ በግ እንደ ግምጋሜህ መጠን ስለ በደል መሥዋዕት ወደ ካህኑ ያምጣ። |
እነዚህ ሁሉ ሚስቶቻቸውን ለመፍታት ቃል በመግባት እጃቸውን ሰጡ፤ ስለ በደላቸውም እያንዳንዳቸው ከመንጋው አንዳንድ አውራ በግ ለበደል መሥዋዕት አቀረቡ።
በሰሜን ትይዩ ያለው ክፍል ደግሞ በመሠዊያው ላይ ለሚያገለግሉ ካህናት ነው። እነዚህም የሳዶቅ ልጆች ሲሆኑ፣ በእግዚአብሔር ፊት ቀርበው ማገልገል የሚችሉ ሌዋውያን እነርሱ ብቻ ናቸው።”
“ካህኑም ከተባዕቱ ጠቦቶች በመውሰድ ከሎግ ዘይቱ ጋራ የበደል መሥዋዕት አድርጎ ያቅርብ፤ የሚወዘወዝ መሥዋዕት በማድረግም በእግዚአብሔር ፊት ይወዝውዛቸው።
“ማንኛውም ሰው ለእግዚአብሔር ባይታመን፤ ከተቀደሰ ከማናቸውም ነገር በማጕደል ኀጢአት ቢሠራ፣ ከመንጋው እንከን የሌለበትን አውራ በግ የበደል መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር ያቅርብ። የዋጋውም ግምት በቤተ መቅደሱ ሰቅል መሠረት ተመዝኖ በጥሬ ብር ይሁን፤ ይህም የበደል መሥዋዕት ነው።
እርሱም ከመንጋው ለበደል መሥዋዕት የሚሆን እንከን የሌለበት አውራ በግ ወደ ካህኑ ያምጣ፤ ዋጋውም ተመጣጣኝ ይሁን። ካህኑም በዚህ ሁኔታ ሰውየው ሳያውቅ ስለ ፈጸመው ስሕተት ያስተሰርይለታል፤ ሰውየውም ይቅር ይባላል።
“ ‘ሰውየው ስለ ሠራው ኀጢአት በግ ለማቅረብ ዐቅሙ ካልፈቀደ ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት የዋኖስ ጫጩቶች የመጀመሪያውን ለኀጢአት መሥዋዕት፣ ሁለተኛውን ለሚቃጠል መሥዋዕት ለእግዚአብሔር ያቅርብ።