ዘሌዋውያን 4:14 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሕዝቡ ጉባኤ ኀጢአት መሥራቱን በተረዳ ጊዜ፣ ለኀጢአት መሥዋዕት የሚሆን አንድ ወይፈን በመገናኛው ድንኳን ፊት ያቅርብ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሠሩትም ኃጢአት ሲታወቅ ጉባኤው ስለ ኃጢአት መሥዋዕት ከመንጋው ወይፈንን ያቀርባሉ፤ ወደ መገናኛውም ድንኳን ፊት ያመጡታል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የተሠራው ኃጢአት እንደ ታወቀ ወዲያውኑ ማኅበሩ ስለ ኃጢአት መሥዋዕት የሚሆን አንድ ወይፈን ያምጣ፤ እርሱንም ወደ መገናኛው ድንኳን ፊት ለፊት ያቅርቡት፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚህም በኋላ፥ የሠሩት ኀጢአት ቢታወቃቸውና ንስሓ ቢገቡ ማኅበሩ ስለ ኀጢአት መሥዋዕት ወይፈንን ያቀርባሉ፤ ወደ ምስክሩም ድንኳን ፊት ያመጡታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህም ቢበድሉ፥ የሠሩት ኃጢአት ሲታወቅ ጉባኤው ስለ ኃጢአት መሥዋዕት ወይፈንን ያቀርባሉ፤ ወደ መገናኛውም ድንኳን ፊት ያመጡታል። |
“ ‘የተቀባውም ካህን በሕዝቡ ላይ በደል የሚያስከትል ኀጢአት ቢሠራ፣ ስለ ሠራው ኀጢአት እንከን የሌለበት አንድ ወይፈን ለእግዚአብሔር የኀጢአት መሥዋዕት አድርጎ ያቅርብ።