“አክዓብ ራሱን በፊቴ እንዴት እንዳዋረደ አየህን? ራሱን ስላዋረደ ይህን መከራ በዘመኑ አላመጣበትም፤ ነገር ግን ይህን በቤቱ ላይ የማመጣው በልጁ ዘመን ነው።”
ዘሌዋውያን 26:41 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይኸውም፣ እኔ ጠላት እንድሆንባቸውና ወደ ጠላቶቻቸው ምድር እንድሰድዳቸው ያደረገኝን ኀጢአት ቢናዘዙ፣ ያልተገረዘው ልባቸው ቢዋረድና ስለ ኀጢአታቸው የሚገባውን ቅጣት ቢቀበሉ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔም ደግሞ እነርሱን በመቃወም እሄዳለሁ፤ ወደ ጠላቶቻቸውም ምድር አመጣቸዋለሁ፤ ነገር ግን በዚያን ጊዜ ያልተገረዘው ልባቸው ቢዋረድ፥ የበደላቸውንም ቅጣት ቢቀበሉ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱን ተቃውሜ ወደ ጠላቶቻቸው አገር እንዲሰደዱ አደረግሁ፤ ሆኖም እልኸኛ ልባቸው በትሕትና ተሰብሮ ከኃጢአታቸው ቢታረሙ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔም ደግሞ አግድሜ ከእነርሱ ጋር በቍጣ ሄድሁ፤ በጠላቶቻቸውም ምድር አጠፋቸዋለሁ። ነገር ግን በዚያን ጊዜ ያልተገረዘው ልባቸው ያፍራል፤ ስለ ኀጢአታቸውም ይናዘዛሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔም ደግሞ በእንቢተኝነት ሄድሁባቸው፤ ወደ ጠላቶቻቸውም ምድር አገባኋቸው፤ ነገር ግን በዚያን ጊዜ ያልተገረዘው ልባቸው ቢዋረድ፥ የኃጢአታቸውንም ቅጣት ቢቀበሉ፥ |
“አክዓብ ራሱን በፊቴ እንዴት እንዳዋረደ አየህን? ራሱን ስላዋረደ ይህን መከራ በዘመኑ አላመጣበትም፤ ነገር ግን ይህን በቤቱ ላይ የማመጣው በልጁ ዘመን ነው።”
ሮብዓም ራሱን ዝቅ አድርጎ ስላዋረደ፣ የእግዚአብሔር ቍጣ ከርሱ ተመለሰ፤ ፈጽሞም አላጠፋውም። በይሁዳም ደግሞ በጥቂቱም ቢሆን መልካም ነገር ተገኝቶ ነበር።
ይሁን እንጂ ሕዝቅያስና የኢየሩሳሌም ሕዝብ ስለ ልባቸው ትዕቢት ራሳቸውን አዋረዱ፤ ስለዚህ የእግዚአብሔር ቍጣ በዘመነ መንግሥቱ አልመጣባቸውም።
ጸሎቱና እግዚአብሔር ራርቶ ልመናውን እንዴት እንደ ተቀበለው፣ ኀጢአቱ ሁሉና ታማኝነቱን ማጕደሉ፣ እንደዚሁም ራሱን ከማዋረዱ በፊት ያሠራቸው የኰረብታ መስገጃ ስፍራዎች፣ ያቆማቸው የአሼራ ምስል ዐምዶችና ጣዖታት ሁሉ በባለራእዮች መዛግብት ተጽፈዋል።
“ይህ ሁሉ የደረሰብን በክፉ ሥራችንና በብዙ በደላችን ምክንያት ነው፤ አምላካችን ሆይ፤ አንተ ግን እንደ በደላችን ብዛት አልቀጣኸንም፤ ይልቁንም ቅሬታን ተውህልን።
የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ጻድቅ ነህ፤ እኛም በዚህ ዕለት ተርፈን በሕይወት አለን። እነሆ፣ በፊትህ ከነበደላችን ቀርበናል፤ ከበደላችን የተነሣ ግን በፊትህ ሊቆም የሚችል ማንም የለም።”
ሙሴና አሮን ወደ ፈርዖን ሄደው እንዲህ አሉት፤ “የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ራስህን በፊቴ ለማዋረድ እስከ መቼ እንቢ ትላለህ? ሕዝቤ ያመልኩኝ ዘንድ ልቀቃቸው።
እናንተ የይሁዳ ሰዎች፣ የኢየሩሳሌምም ነዋሪዎች፤ ለእግዚአብሔር ተገረዙ፤ የልባችሁንም ሸለፈት አስወግዱ፤ አለዚያ ስለ ሠራችሁት ክፋት፣ ቍጣዬ እንደ እሳት ይንበለበላል፤ ሊገታውም የሚችል የለም።
ለማን ልናገር? ማንን ላስጠንቅቅ? ማንስ ይሰማኛል? እነሆ፣ ጆሮዎቻቸው አልተገረዙምና፣ መስማት አይችሉም። በእግዚአብሔር ቃል ይሣለቃሉ፤ ደስም አይሰኙበትም።
አካሄዳቸውንና ተግባራቸውን በምታዩበት ጊዜ፣ ትጽናናላችሁ፤ አንዳች ነገር በከንቱ እንዳላደረገሁ ትረዳላችሁና፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።’ ”
ከአስጸያፊ ሥራችሁም ሌላ ምግብ፣ ሥብና ደም ስታቀርቡ ልባቸውንና ሥጋቸውን ያልተገረዙትን እንግዶች ወደ መቅደሴ በማስገባት ቤተ መቅደሴን አረከሳችሁ፤ ቃል ኪዳኔንም አፈረሳችሁ።
እነዚህ ከሰይፍ የተረፉት፣ ከእኔ ዘወር ባለ አመንዝራ ልባቸውና ጣዖትን በተከተለ አመንዝራ ዐይናቸው የቱን ያህል እንዳሳዘኑኝ፤ በአሕዛብ ምድር ሆነው ያስታውሱኛል፤ ካደረጉት ክፋትና ከፈጸሙት ርኩስ ተግባር ሁሉ የተነሣም ራሳቸውን ይጸየፋሉ።
“እላችኋለሁ፤ ከፈሪሳዊው ይልቅ ይህኛው በእግዚአብሔር ዘንድ ጻድቅ ተብሎ ወደ ቤቱ ተመለሰ፤ ራሱን ከፍ ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ዝቅ ይላልና፤ ራሱን ዝቅ ዝቅ የሚያደርግ ግን ከፍ ይላል።”
አምላክህን እግዚአብሔርን በፍጹም ልብህና በፍጹም ነፍስህ እንድትወድደው፣ በሕይወትም እንድትኖር፣ አምላክህ እግዚአብሔር የአንተንና የዘርህን ልብ ይገርዛል።
ብዙ ጥፋትና የከፋ ችግር በደረሰባቸው ጊዜ ይህ መዝሙር ምስክር ይሆንባቸዋል፤ በዘሮቻቸው የሚረሳ አይደለምና። ወደ ማልሁላቸው ምድር ሳላስገባቸው በፊት ምን ለማድረግ እንደሚያስቡ እንኳ አስቀድሜ ዐውቃለሁ።”