ዘሌዋውያን 23:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ለእስራኤላውያን እንዲህ ብለህ ተናገር፤ ‘የተቀደሱ ጉባኤዎች ብላችሁ የምትዋጇቸው የእግዚአብሔር በዓላት እነዚህ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ለእነርሱ ተናገር፦ የተቀደሱ ጉባኤዎች ብላችሁ የምታውጁአቸው በዓላቶቼ፥ የጌታ በዓላት፥ እነዚህ ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ለእስራኤል ሕዝብ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ የተቀደሱ ብላችሁ የምታውጁአቸው የእኔ የእግዚአብሔር በዓላት እነዚህ ናቸው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ቅዱሳት ጉባኤያት ብላችሁ የምትጠሩአቸው በዓላቴ፥ የእግዚአብሔር በዓላት እነዚህ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ የተቀደሰ ጉባኤ ብላችሁ የምታውጁአቸው በዓላቶቼ፥ የእግዚአብሔር በዓላት፥ እነዚህ ናቸው። |
እንዲሁም በየሰንበቱ፣ በወር መባቻ በዓልና በተደነገጉት በዓላት ሁሉ፣ የሚቃጠል መሥዋዕት ለእግዚአብሔር በሚቀርብበት ጊዜ ይፈጽሙ ነበር፤ በተወሰነላቸው ቍጥርና በተሰጠውም መመሪያ መሠረት፣ ዘወትር በእግዚአብሔር ፊት ያገለግሉ ነበር።
ከዚህ በኋላ፣ ሰሎሞን ለጢሮስ ንጉሥ ለኪራም የሚከተለውን ይህን መልእክት ላከ፤ “አባቴ ዳዊት የሚኖርበትን ቤተ መንግሥት ሲሠራ እንደ ላክህለት ሁሉ፣ ለእኔም የዝግባ ዕንጨት ላክልኝ።
ስለዚህ የእስራኤልን አምላክ የእግዚአብሔርን ፋሲካ ለማክበር ሕዝቡ ከመላው ኢየሩሳሌም እንዲመጣ፣ ከቤርሳቤህ እስከ ዳን ድረስ ዐዋጅ እንዲነገር ወሰኑ፤ በተጻፈው መሠረት በዓሉ ብዛት ባለው ሕዝብ ተከብሮ አያውቅም ነበርና።
ከዚያም በኋላ መደበኛውን የሚቃጠል መሥዋዕት፣ የወር መባቻን መሥዋዕት፣ በተቀደሱት የእግዚአብሔር በዓላት የሚቀርበውን መሥዋዕትና የበጎ ፈቃድ ስጦታ ለእግዚአብሔር አቀረቡ።
በዓላታችንን የምናከብርባትን ከተማ ጽዮንን ተመልከት፤ ሰላማዊ መኖሪያ፣ የማትነቃነቅ ድንኳን የሆነችውን፣ ካስማዋ የማይነቀል፣ ከገመዷ አንዱ እንኳ የማይበጠሰውን፣ ኢየሩሳሌምን ዐይኖችህ ያያሉ።
የጽዮን መንገዶች ያለቅሳሉ፤ በዓላቷን ለማክበር የሚመጣ የለምና፤ በበሮቿ ሁሉ የሚገባና የሚወጣ የለም፤ ካህናቷ ይቃትታሉ፤ ደናግሏ ክፉኛ ዐዝነዋል፤ እርሷም በምሬት ትሠቃያለች።
“ ‘በማንኛውም ክርክር ካህናት ዳኞች ሆነው ያገልግሉ፤ በሥርዐቴም መሠረት ይወስኑ። የተለዩ በዓላቴን የሚመለከቱ ሕጎቼንና ሥርዐቶቼን ሁሉ ይጠብቁ፤ ሰንበታቴንም ቅዱስ አድርገው ይጠብቁ።
ቅዱስ ጾምን ዐውጁ፤ የተቀደሰንም ጉባኤ ጥሩ፤ ሽማግሌዎችን ሰብስቡ፤ በምድሪቱ የሚኖሩትን ሁሉ፣ ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር ቤት ጥሩ፤ ወደ እግዚአብሔርም ጩኹ።
በዚያ ዕለት የተቀደሰ ጉባኤ ዐውጁ፤ የተለመደ ተግባራችሁንም አታከናውኑ፤ ይህም በምትኖሩበት ስፍራ ሁሉ ለሚመጡት ትውልዶች የዘላለም ሥርዐት ነው።
“ ‘የሚቃጠል መሥዋዕትንና የእህል ቍርባንን፣ መሥዋዕትንና የመጠጥ ቍርባንን በተመደበላቸው ቀን ለእግዚአብሔር በእሳት ለማቅረብ፣ የተቀደሱ ጉባኤዎችን የምታውጁባቸው የእግዚአብሔር በዓላት እነዚህ ናቸው።
እነሆ፤ የምሥራች የሚያመጣው፣ ሰላምን የሚያውጀው ሰው እግር፣ በተራሮች ላይ ነው፤ ይሁዳ ሆይ፤ በዓላትህን አክብር፤ ስእለትህንም ፈጽም፤ ከእንግዲህ ምናምንቴ ሰዎች አይወርሩህም፤ እነርሱም ፈጽመው ይጠፋሉ።
እንዲሁም በደስታችሁ ቀናት ማለት በተደነገጉት በዓሎቻችሁና የወር መባቻ በዓል ስታከብሩ በሚቃጠል መሥዋዕታችሁና በኅብረት መሥዋዕታችሁ ላይ መለከቱን ንፉ፤ እነዚህም በአምላካችሁ ፊት መታሰቢያ ይሆኑላችኋል። እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።”
“ ‘ከስእለትና ከበጎ ፈቃድ ስጦታዎቻችሁ በተጨማሪ፣ የሚቃጠሉ መሥዋዕቶቻችሁን፣ የእህል ቍርባኖቻችሁን፣ የመጠጥ ቍርባኖቻችሁንና የኅብረት መሥዋዕቶቻችሁን በበዓላታችሁ ለእግዚአብሔር አቅርቡ።’ ”