ዘሌዋውያን 17:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ እስራኤላውያንን፣ “ከእናንተ ማንም ደም አይብላ፤ በመካከላችሁ የሚኖር መጻተኛም ቢሆን ደም አይብላ” አልሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ለእስራኤል ልጆች እንዲህ አልሁ፦ ከእናንተ ማንም ሰው ደምን አይብላ፥ በመካከላችሁም ከሚኖር እንግዳ ማንም ሰው ደምን አይብላ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ለእስራኤላውያን የምለው ይህ ነው፤ ከእናንተ ማንም፥ ወይም በመካከላችሁ ከሚኖሩ ማንኛውም መጻተኛ ደም መብላት የለበትም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ የእስራኤልን ልጆች፦ ‘ከእናንተ ማንም ደምን አይበላም፤ በመካከላችሁም ከሚኖሩ እንግዶች ማንም ደምን አይበላም’ አልሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ የእስራኤልን ልጆች፦ ከእናንተ ማንም ደምን አይበላም፥ በመካከላችሁም ከሚኖሩ እንግዶች ማንም ደምን አይበላም አልሁ። |
ስለዚህ እንዲህ በላቸው፣ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ሥጋውን ከነደሙ ትበላላችሁ፤ ዐይኖቻችሁንም ወደ ጣዖቶቻችሁ ታነሣላችሁ፤ ደምም ታፈስሳላችሁ፤ ታዲያ በዚህ ሁኔታ ምድሪቱን ልትወርሱ ታስባላችሁ?
የፍጡር ሕይወት በደሙ ውስጥ ነውና፤ በመሠዊያ ላይ ለሕይወታችሁ ማስተስረያ እንዲሆን ደሙን ሰጥቻችኋለሁ፤ ለሰውም ሕይወት ስርየት የሚያስገኝ ደም ነው።
“ ‘እንዲበላ የተፈቀደውን ማንኛውንም እንስሳ ወይም ወፍ ዐድኖ የያዘ ማንኛውም እስራኤላዊ ወይም በመካከላችሁ የሚኖር ማንኛውም መጻተኛ ደሙን ከውስጡ ያፍስስ፤ ዐፈርም ያልብሰው፤