ዘሌዋውያን 16:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሮንም አንዱን ዕጣ ለእግዚአብሔር፣ ሌላውን ለሚለቀቀው ፍየል ለማድረግ በሁለቱ ፍየሎች ላይ ዕጣ ይጣል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሮንም በሁለቱ ፍየሎች ላይ ዕጣ ይጥልባቸዋል፥ አንዱ ዕጣ ለጌታ ሌላው ዕጣ ለዐዛዜል ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያም አንዱ ‘ለእግዚአብሔር’ ሁለተኛው ‘ለዐዛዜል’ የሚል ምልክት ያለባቸው ሁለት ድንጋዮች ወስዶ ዕጣ ያውጣ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሮንም በሁለቱ የፍየል ጠቦቶች ላይ ዕጣ ይጥልባቸዋል፤ አንዱን ዕጣ ለእግዚአብሔር፥ ሌላውንም ዕጣ ለሚለቀቅ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሮንም በሁለቱ ፍየሎች ላይ ዕጣ ይጥልባቸዋል፥ አንዱን ዕጣ ለእግዚአብሔር ሌላውንም ዕጣ ለሚለቀቅ። |
ከዚያም መርከበኞቹ እርስ በርሳቸው፣ “ይህ ክፉ ነገር በማን ምክንያት እንደ መጣብን ለማወቅ፣ ኑ ዕጣ እንጣጣል” ተባባሉ። ዕጣም ተጣጣሉ፤ ዕጣውም በዮናስ ላይ ወደቀ።
ምድሪቱንም በየጐሣዎቻችሁ በዕጣ ተከፋፈሉ። ከፍ ያለ ቍጥር ላለው ሰፋ ያለውን፣ ዝቅተኛ ቍጥር ላለው ደግሞ አነስተኛውን ስጡ፤ ምንም ይሁን ምን በዕጣ የወጣላቸው፣ የየራሳቸው ርስት ይሆናል። አከፋፈሉም በየአባቶቻችሁ ነገዶች አንጻር ይሁን።