ዘሌዋውያን 13:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀይ ሥጋ ተለውጦ ከነጣ ግን ወደ ካህኑ ይሂድ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሚያዠው ሥጋ ግን ተለውጦ ቢነጣ እንደገና ወደ ካህኑ ይመጣል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቊስሉ ቢፈወስና እንደገና ወደ ነጭነት ቢለወጥ ግን እንደገና ወደ ካህኑ ይሄዳል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጤነኛው ቆዳ ተመልሶ ቢነጣ እንደገና ወደ ካህኑ ይመጣል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሚያዠውም ሥጋ ተለውጦ ቢነጣ እንደ ገና ወደ ካህኑ ይመጣል። |
ኢየሱስ ከከተሞች በአንዱ በነበረበት ጊዜ፣ አንድ ለምጽ የወረሰው ሰው በዚያው ከተማ ነበር፤ ይህ ሰው ኢየሱስን ባየው ጊዜ በፊቱ ተደፋና፣ “ጌታ ሆይ፤ ብትፈቅድ እኮ ልታነጻኝ ትችላለህ” ብሎ ለመነው።