ዘሌዋውያን 11:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክንፍና ቅርፊት የሌለው ማንኛውም በውሃ ውስጥ የሚኖር ፍጡር በእናንተ ዘንድ አስጸያፊ ይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በውኃ ውስጥ የሚኖሩ ክንፍና ቅርፊት የሌላቸው ሁሉ በእናንተ ዘንድ የተጸየፉ ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ በውሃ ውስጥ የሚኖሩ ክንፍና ቅርፊት የሌላቸው ፍጥረቶች ሁሉ በእናንተ ዘንድ የተጠሉ ይሁኑ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ክንፍና ቅርፊትም የሌላቸው በውኃ ውስጥ የሚኖሩት ሁሉ ለእናንተ ርኩሳን ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ክንፍና ቅርፊትም የሌላቸው በውኃ ውስጥ የሚኖሩት ሁሉ በእናንተ ዘንድ የተጸየፉ ናቸው። |