ዘሌዋውያን 10:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም መጥተው ሙሴ ባዘዛቸው መሠረት፣ ሟቾቹ የክህነት ቀሚሳቸውን እንደ ለበሱ ተሸክመው ከሰፈር ወደ ውጭ አወጧቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም እንደ ተናገረው ቀርበው ቀሚሳቸውን ይዘው አነሡአቸው፥ ከሰፈሩም ውጭ ወሰዱአቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም ልብሰ ተክህኖአቸውን ሳያወልቁ መጥተው ሬሳዎቹን ሙሴ ባዘዛቸው መሠረት ከሰፈር ወደ ውጪ አወጡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም ገብተው አነሡአቸው፤ ሙሴም እንዳለ በልብሳቸው ከሰፈር ወደ ውጭ ወሰዱአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም ቀርበው አነሡአቸው፥ ሙሴም እንዳለ በቀሚሳቸው ከሰፈር ወደ ውጭ ወሰዱአቸው። |
ልብሶቹን ወስደህ ለአሮን አልብሰው፤ እጀ ጠባብ፣ የኤፉድ ቀሚስ፣ ኤፉዱንና የደረት ኪሱን አልብሰው፤ ኤፉዱን በርሱ ላይ በጥበብ በተሠራ መታጠቂያ እሰረው።
እግዚአብሔርም ባዘዘው መሠረት ሙሴ፣ የአሮንን ልጆች ወደ ፊት አቅርቦ እጀ ጠባብ አለበሳቸው፤ መታጠቂያዎችን አስታጠቃቸው፤ ቆብም ደፋላቸው።