La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘሌዋውያን 10:18 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ደሙ ወደ ተቀደሰው ስፍራ ስላልገባ፣ በሰጠሁት ትእዛዝ መሠረት ፍየሉን በተቀደሰው ስፍራ መብላት ይገባችሁ ነበር።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እነሆ፥ ደሙን ወደ መቅደሱ ውስጥ አላገባችሁትም፤ እኔ እንደ ታዘዝሁ በቅዱሱ ስፍራ ውስጥ ትበሉት ይገባችሁ ነበር።”

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ደሙ ወደተቀደሰው ድንኳን ስላልገባ እኔ ባዘዝኳችሁ መሠረት በዚያው በተቀደሰው ስፍራ የቀረበውን መሥዋዕት መመገብ ነበረባችሁ።”

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እነሆ፥ ደሙን ወደ መቅ​ደስ ውስጥ አላ​ገ​ባ​ች​ሁ​ትም፤ እኔ እን​ደ​ታ​ዘ​ዝሁ በቅ​ዱስ ስፍራ ውስጥ ትበ​ሉት ዘንድ ይገ​ባ​ችሁ ነበር።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እነሆ ደሙን ወደ መቅደሱ ውስጥ አላገባችሁትም፤ እኔ እንዳዘዝሁ በቅዱሱ ስፍራ ውስጥ ትበሉት ዘንድ ይገባችሁ ነበር አላቸው።

Ver Capítulo



ዘሌዋውያን 10:18
4 Referencias Cruzadas  

ለክህነታቸውና ለመቀደሳቸው ማስተስረያ የሆኑትን እነዚህን መሥዋዕቶች ይብሉ፤ የተቀደሱ ስለ ሆኑ ሌላ ማንም አይብላቸው።


እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ አለው፤


መሥዋዕቱንም የሚያቀርበው ካህን ይብላው፤ ይህም በተቀደሰው ስፍራ በመገናኛው ድንኳን ቅጥር ግቢ ውስጥ፣ በአደባባዩ ላይ ይበላ።


ነገር ግን ደሙ ማስተስረያ እንዲሆን ወደ መገናኛው ድንኳን ወደ ቅድስት የቀረበው የኀጢአት መሥዋዕት ሁሉ በእሳት ይቃጠል እንጂ አይበላ።