ዘሌዋውያን 10:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴ ለኀጢአት መሥዋዕት የሚቀርበውን ፍየል አጥብቆ ፈለገ፤ መቃጠሉንም በተረዳ ጊዜ የተረፉትን የአሮንን ልጆች አልዓዛርንና ኢታምርን ተቈጣቸው፤ እንዲህም አላቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም የኃጢአት መሥዋዕት ስለ ሆነው ፍየል አጥብቆ ጠየቀ፥ እነሆም ተቃጥሎ ነበር፤ ሙሴም የተረፉትን የአሮንን ልጆች አልዓዛርንና ኢታምርን እንዲህ ብሎ ተቆጣ፦ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴ ስለ ኃጢአት ስርየት መሥዋዕት በመሆን ቀርቦ የነበረውን ፍየል ምን እንዳደረጉት በጠየቀ ጊዜ ተቃጥሎ እንደ ነበር ተረዳ፤ ይህም ነገር በአልዓዛርና በኢታማር ላይ ሙሴን ስላስቈጣው እንዲህ ሲል ጠየቀ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም የኀጢአቱን መሥዋዕት ፍየል እጅግ ፈለገው፤ በፈለገውም ጊዜ እነሆ ተቃጥሎ ነበር፤ ሙሴም የቀሩትን የአሮንን ልጆች አልዓዛርንና ኢታምርን ተቈጣቸው፤ እንዲህም አላቸው፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም የኃጢያቱን መሥዋዕት ፍየል እጅግ ፈለገው፥ እነሆም ተቃጥሎ ነበር፤ ሙሴም የቀሩትን የአሮንን ልጆች አልአዛርንና ኢታምርን ተቆጥቶ፦ |
ያለ እርሾ መጋገር አለበት፤ በእሳት ከሚቀርብልኝ ቍርባን ይህን የእነርሱ ድርሻ አድርጌ ሰጥቻቸዋለሁ። ይህም፣ እንደ ኀጢአት መሥዋዕትና እንደ በደል መሥዋዕት ሁሉ እጅግ የተቀደሰ ነው።
አሮንም የሕዝቡን መሥዋዕት አቀረበ፤ ስለ ሕዝቡ የኀጢአት መሥዋዕት የሆነውን ፍየል ወስዶ ዐረደው፤ እንደ ፊተኛው ሁሉ ይህንም በኀጢአት መሥዋዕትነት ሠዋው።
እስራኤላውያንንም እንዲህ በላቸው፤ ‘ለኀጢአት መሥዋዕት አንድ አውራ ፍየል፣ ለሚቃጠል መሥዋዕት እንከን የሌለባቸውን የአንድ ዓመት እንቦሳና የአንድ ዓመት ጠቦት፣
እኔ ግን እላችኋለሁ፤ ወንድሙን ያለ አግባብ የሚቈጣ ይፈረድበታል፤ ማንም ወንድሙን ‘ጅል’ የሚል በሸንጎ ፊት ይጠየቅበታል፤ ‘ደደብ’ የሚለው ደግሞ የገሃነመ እሳት ፍርድ ይጠብቀዋል።
ኢየሱስም ይህን ሲያይ ተቈጥቶ እንዲህ አላቸው፤ “ሕፃናት ወደ እኔ እንዲመጡ ፍቀዱላቸው፤ አትከልክሏቸውም፤ የእግዚአብሔር መንግሥት እንደ እነዚህ ላሉት ናትና።
በልባቸው ደንዳናነት ዐዝኖ በዙሪያው የቆሙትን በቍጣ ተመለከታቸውና ሰውየውን፣ “እጅህን ዘርጋ!” አለው፤ ሰውየውም እጁን ዘረጋ፤ እጁም ፍጹም ደኅና ሆነችለት።