ሰቈቃወ 5:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ባሮች ሠልጥነውብናል፤ ከእጃቸው ነጻ የሚያወጣን ማንም የለም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባርያዎች ሠልጥነውብናል፥ ከእጃቸው የሚታደገን የለም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባሪያዎች ይገዙናል፤ ከእጃቸውም ሊያድነን የሚችል የለም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባሪያዎች ሠልጥነውብናል፤ ከእጃቸውም የሚታደገን የለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባሪያዎች ሠልጥነውብናል፥ ከእጃቸው የሚታደገን የለም። |
ነገር ግን ሖሮናዊው ሰንባላጥ፣ አሞናዊው ሹም ጦቢያና ዐረባዊው ጌሳም ይህን ሲሰሙ አፌዙብን፤ አንቋሸሹንም፤ እንዲሁም፣ “የምታደርጉት ይህ ምንድን ነው? በንጉሡ ላይ ልታምፁ ትፈልጋላችሁን?” አሉ።
ከእኔ በፊት የነበሩት የቀድሞዎቹ አገረ ገዦች ግን ከምግቡና ከወይኑ ሌላ፣ በሕዝቡ ላይ ከባድ ሸክም በመጫን አርባ ሰቅል ብር ይወስዱ ነበር፤ ረዳቶቻቸውም እንዲሁ ይጭኑባቸው ነበር። እኔ ግን እግዚአብሔርን ከመፍራቴ የተነሣ እንዲህ ያለውን አላደረግሁም።
ከእንግዲህ በምድሪቱ ለሚኖረው ሕዝብ አልራራምና” ይላል እግዚአብሔር፤ “ሰውን ሁሉ ለባልንጀራውና ለንጉሡ አሳልፌ እሰጣለሁ፤ እነርሱ ምድሪቱን ያስጨንቃሉ፤ እኔም ከእጃቸው አላድናቸውም።”