ሰቈቃወ 4:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሁን ግን ከጥላሸት ይልቅ ጠቍረዋል፤ በመንገድም የሚያውቃቸው የለም፤ ቈዳቸው ከዐጥንታቸው ጋራ ተጣብቋል፤ እንደ ዕንጨትም ደርቀዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሔት። ፊታቸው ከጥቀርሻ ይልቅ ጠቁሮአል፥ በመንገድም አልታወቁም፥ ቁርበታቸው ወደ አጥንታቸው ተጣብቆአል፥ ደርቆአል፥ እንደ እንጨት ሆኖአል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሁን ግን ፊታቸው እንደ ጥላሸት ስለ ጠቈረ፥ በየመንገዱ ወድቀው ሲገኙ የሚያውቃቸው የለም፤ እንደ እንጨት የደረቀ ቆዳቸው በአጥንታቸው ላይ ተጣብቆአል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሔት። ፊታቸው ከጥቀርሻ ይልቅ ጠቍሮአል፤ በመንገድም አልታወቁም፤ ቍርበታቸው ወደ አጥንታቸው ተጣብቆአል፤ ደርቆአል፤ እንደ እንጨትም ሆኖአል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሔት። ፊታቸው ከጥቀርሻ ይልቅ ጠቍሮአል፥ በመንገድም አልታወቁም፥ ቁርበታቸው ወደ አጥንታቸው ተጣብቆአል፥ ደርቆአል፥ እንደ እንጨት ሆኖአል። |
እነርሱም ከሩቅ ሆነው ሲመለከቱት እርሱ መሆኑን ሊለዩ አልቻሉም፤ በዚህ ጊዜ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው አለቀሱ፤ ልብሳቸውንም ቀድደው በራሳቸው ላይ ትቢያ ነሰነሱ።
‘ለማስጠንቀቂያ እንዲሆናችሁ በእግራችን ላይ ያለውን የከተማችሁን ትቢያ እንኳ እናራግፍላችኋለን፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር መንግሥት ቀርባለች ይህን ዕወቁ።’