እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፤ “ነቢያቱ በስሜ የሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፤ እኔ አልላክኋቸውም፤ አላዘዝኋቸውም፤ አልተናገርኋቸውምም። የሐሰት ራእይ፣ ሟርት፣ ከንቱ ነገርንና የልባቸውን ሽንገላ ይተነብዩላችኋል።
ሰቈቃወ 4:13 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህ ግን ከነቢያት ኀጢአት፣ ከካህናቷም መተላለፍ የተነሣ ሆኗል፤ በውስጧ፣ የጻድቃንን ደም አፍስሰዋልና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሜም። የጻድቃንን ደም በውስጥዋ ስላፈሰሱ ስለ ነቢዮችዋ ኃጢአትና ስለ ካህናቶች በደል ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም የሆነው በመካከልዋ የንጹሓንን ደም ባፈሰሱት በካህናትዋ በደልና በነቢያትዋ ኃጢአት ምክንያት ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሜም። የጻድቃንን ደም በውስጥዋ ስላፈሰሱ፥ ስለ ነቢያቷ ኀጢአትና ስለ ካህናቷ በደል ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሜም። የጻድቃንን ደም በውስጥዋ ስላፈሰሱ ስለ ነቢያቶችዋ ኃጢአትና ስለ ካህናቶች በደል ነው። |
እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፤ “ነቢያቱ በስሜ የሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፤ እኔ አልላክኋቸውም፤ አላዘዝኋቸውም፤ አልተናገርኋቸውምም። የሐሰት ራእይ፣ ሟርት፣ ከንቱ ነገርንና የልባቸውን ሽንገላ ይተነብዩላችኋል።
“ከጥንት ጀምሮ ቀንበርሽን ሰበርሁ፤ እስራትሽን በጣጠስሁ፤ አንቺም፣ ‘አላገለግልህም’ አልሽ፤ ከፍ ባለውም ኰረብታ ሁሉ ሥር፣ በእያንዳንዱም ለምለም ዛፍ ሥር፣ ለማመንዘር ተጋደምሽ።
ነቢያት በሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፤ ካህናት በነቢያቱ ምክር ያስተዳድራሉ፤ ሕዝቤም እንዲህ ያለውን ይወድዳሉ፤ ፍጻሜው ሲደርስ ግን ምን ታደርጉ ይሆን?”
የነቢያቶችሽ ራእይ፣ ሐሰትና ከንቱ ነው፤ ምርኮኛነትሽን ለማስቀረት፣ ኀጢአትሽን አይገልጡም። የሚሰጡሽም የትንቢት ቃል፣ የሚያሳስትና ከመንገድ የሚያወጣ ነው።
መሳፍንቷ እያገሣ ግዳዩን እንደሚቦጫጭቅ አንበሳ በውስጧ ያሤራሉ፤ ሕዝቡን ይበላሉ፤ ንብረትንና የከበሩ ነገሮችን ይነጥቃሉ፤ ብዙዎችንም ሴቶች መበለት ያደርጋሉ።
ከነቢያት መካከል አባቶቻችሁ ያላሳደዱት ማን አለ? የጻድቁን መምጣት አስቀድመው የተናገሩትን እንኳ ገድለዋል፤ እናንተም አሁን አሳልፋችሁ ሰጣችሁት፤ ገደላችሁትም፤