ሰቈቃወ 3:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሞቱ ብዙ ጊዜ እንደ ሆናቸው፣ በጨለማ እንድኖር አደረገኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቀድሞ ሞተው እንደ ነበሩ በጨለማ አኖረኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከብዙ ጊዜ በፊት እንደ ሞተ ሰው በጨለማ ውስጥ እንድቀመጥ አስገደደኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንደ ቀድሞ ሙታን በጨለማ አኖረኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቀድሞ ሞተው እንደ ነበሩ በጨለማ አኖረኝ። |
በቅጥሩ ላይ እንደ ዕውር ተደናበርን፤ አካሄዳችንም ዐይን እንደሌላቸው በዳበሳ ሆነ፤ ጀንበር በምትጠልቅበት ጊዜ እንደሚሆነው በእኩለ ቀን ተደናበርን፤ በብርቱዎች መካከልም እንደ ሙታን ሆንን።