ሰቈቃወ 2:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ማደሪያውን እንደ አትክልት ስፍራ ባዶ አደረገ፤ መሰብሰቢያ ስፍራውን አፈረሰ፤ እግዚአብሔር ጽዮንን፣ ዓመት በዓላቶቿንና ሰንበታቷን እንድትረሳ አደረጋት፤ በጽኑ ቍጣው፣ ንጉሡንና ካህኑን እጅግ ናቀ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዋው። ማደሪያውን እንደ አትክልት ነቀለ፥ የበዓሉን ስፍራ አጠፋ፥ እግዚአብሔር በጽዮን ዓመት በዓሉንና ሰንበቱን አስረሳ፥ በቁጣውም መዓት ንጉሡንና ካህኑን አቃለለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መቅደሱን በአትክልት ቦታ ውስጥ እንዳለ መጠለያ አወደመ፤ እግዚአብሔር በጽዮን በዓሎችንና ሰንበቶችን አስቀረ፤ በኀይለኛ ቊጣውም ንጉሡንና ካህኑን አዋረደ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዋው። ማደሪያውን እንደ ወይን ጋረደ፤ በዓሉን ሁሉ አጠፋ፤ እግዚአብሔር በጽዮን ያደረገውን በዓሉንና ሰንበቱን አስረሳ፤ በቍጣውም መዓት ነገሥታቱን፥ አለቆቹንና ካህናቱን አጠፋ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዋው። ማደሪያውን እንደ አትክልት ነቀለ፥ የበዓሉን ስፍራ አጠፋ፥ እግዚአብሔር በጽዮን ዓመት በዓሉንና ሰንበቱን አስረሳ፥ በቍጣውም መዓት ንጉሡንና ካህኑን አቃለለ። |
ከንቱውን መባ አታቅርቡ፤ ዕጣናችሁን እጸየፋለሁ፤ የወር መባቻ በዓላችሁን፣ ሰንበቶቻችሁን፣ ጉባኤያችሁንና በክፋት የተሞላውን ስብሰባችሁን መታገሥ አልቻልሁም።
ነገር ግን የሰንበትን ቀን ሳትቀድሱ፣ በሰንበት ቀን ሸክም ተሸክማችሁ በኢየሩሳሌም በሮች በመግባት ትእዛዜን ብትጥሱ፣ በኢየሩሳሌም በሮች ላይ ምሽጎቿን የሚበላ፣ የማይጠፋ እሳት እጭራለሁ።’ ”
የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ ‘ቍጣዬና መዓቴ በኢየሩሳሌም በሚኖሩት ሁሉ ላይ እንደ ፈሰሰ፣ እንዲሁ ወደ ግብጽ በገባችሁ ጊዜ መዓቴ በእናንተ ላይ ይፈስሳል፤ እናንተም የመረገሚያና የድንጋጤ፣ የመረገሚያና የመዘባበቻ ምልክት ትሆናላችሁ፤ ይህንም ስፍራ ዳግመኛ አታዩም።’
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እንዲህ በለው፤ ‘እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ በምድር ሁሉ የገነባሁትን አፈርሳለሁ፤ የተከልሁትን እነቅላለሁ።
እግዚአብሔር አምላካችን የተበቀለውን፣ ስለ ቤተ መቅደሱ የተበቀለውን በቀል፣ ከባቢሎን የመጡ ኰብላዮችና ስደተኞች፣ በጽዮን የሚናገሩትን ስሟቸው።
የጽዮን መንገዶች ያለቅሳሉ፤ በዓላቷን ለማክበር የሚመጣ የለምና፤ በበሮቿ ሁሉ የሚገባና የሚወጣ የለም፤ ካህናቷ ይቃትታሉ፤ ደናግሏ ክፉኛ ዐዝነዋል፤ እርሷም በምሬት ትሠቃያለች።