እንዲሁም ሁለት ምናምንቴ ሰዎች ከፊት ለፊቱ አስቀምጡና፣ ‘እግዚአብሔርንም ንጉሡንም ሰድቧል’ ብለው ይመስክሩበት፤ ከዚያም አውጥታችሁ በድንጋይ ወግራችሁ ግደሉት።”
ዮሐንስ 8:17 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሁለት ሰዎች ምስክርነት ተቀባይነት እንዳለው በሕጋችሁ ተጽፏል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሁለት ሰዎችም ምስክርነት እውነት እንደሆነ በሕጋችሁ ትጽፎአል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሁለት ሰዎች ምስክርነት እውነት እንደ ሆነ በሕጋችሁ ተጽፎአል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሁለት ሰዎች ምስክርነት የታመነ እንደ ሆነ በሕጋችሁ ተጽፎአል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሁለት ሰዎችም ምስክርነት እውነት እንደ ሆነ በሕጋችሁ ትጽፎአል። |
እንዲሁም ሁለት ምናምንቴ ሰዎች ከፊት ለፊቱ አስቀምጡና፣ ‘እግዚአብሔርንም ንጉሡንም ሰድቧል’ ብለው ይመስክሩበት፤ ከዚያም አውጥታችሁ በድንጋይ ወግራችሁ ግደሉት።”
“ ‘ሰው የገደለ ማንኛውም ሰው በሞት የሚቀጣው ምስክሮች ሲመሰክሩበት ብቻ ነው፤ ይሁን እንጂ ማንም ሰው በአንድ ምስክር ብቻ በሞት አይቀጣም።
በማንኛውም ወንጀል ወይም ሕግ በመተላለፍ ሰውን ጥፋተኛ ለማድረግ፣ አንድ ምስክር አይበቃም፤ ነገር በሁለት ወይም በሦስት ሰዎች የምስክር አፍ መረጋገጥ አለበት።