በዚያ ጊዜ ኢየሱስ እንዲህ አለ፤ “የሰማይና የምድር ጌታ አባት ሆይ፤ ይህን ከጥበበኞችና ከዐዋቂዎች ሰውረህ ለሕፃናት ስለ ገለጥህላቸው አመሰግንሃለሁ፤
ዮሐንስ 7:48 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለመሆኑ ከባለሥልጣኖችና ከፈሪሳውያን በርሱ ያመነ አለ? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከአለቆች ወይም ከፈሪሳውያን በእርሱ ያመነ አለን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለመሆኑ ከባለ ሥልጣኖች ወይም ከፈሪሳውያን በእርሱ ያመኑ አሉን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከአለቆች ወይም ከፈሪሳውያን ያመነበት አለን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከአለቆች ወይስ ከፈሪሳውያን በእርሱ ያመነ አለን? |
በዚያ ጊዜ ኢየሱስ እንዲህ አለ፤ “የሰማይና የምድር ጌታ አባት ሆይ፤ ይህን ከጥበበኞችና ከዐዋቂዎች ሰውረህ ለሕፃናት ስለ ገለጥህላቸው አመሰግንሃለሁ፤
ይህም ቢሆን፣ ከአለቆች መካከል እንኳ ሳይቀር ብዙዎች በርሱ አመኑ፤ ይሁን እንጂ ፈሪሳውያን ከምኵራብ እንዳያስወጧቸው ስለ ፈሩ ማመናቸውን አይገልጡም ነበር።